Connect with us

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ለጥቃት ተጋላጭ ለሆኑ ዞኖች ነዋሪዎችን ማስታጠቅ ጀመረ

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ለጥቃት ተጋላጭ ለሆኑ ዞኖች ነዋሪዎችን ማስታጠቅ ጀመረ
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ለጥቃት ተጋላጭ ለሆኑ ዞኖች ነዋሪዎችን ማስታጠቅ ጀመረ

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ለጥቃት ተጋላጭ ለሆኑ ዞኖች ነዋሪዎችን ማስታጠቅ ጀመረ

በሦስት ቀናት ሥልጠና 1,282 ነዋሪዎች ታጥቀዋል

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በማኅበረሰቦች ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን ለመከላከል፣ በተመረጡ ለጥቃት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎችን አሠልጥኖ ማስታጠቅ መጀመሩን ይፋ አደረገ፡፡

ከጳጉሜን 2012 ዓ.ም. አንስቶ ተደጋጋሚ ጥቃቶች በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በተለይም በመተከል ዞን በመፈጸማቸው የክልሉ መንግሥትና የፌዴራል መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች፣ የመከላከያ ሠራዊትን ጨምሮ ቢያስማራም ጥቃቱን ማስቆም አልተቻለም፡፡ ባለፈው ሁለትና ሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በተሰነዘረ ጥቃት ወደ ሃምሳ የሚጠጉ ሰላማዊ ነዋሪዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ይህንንም ተከትሎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን፣ ችግሩ በክልሉ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ባሉ አመራሮች ጭምር ታግዞ የሚፈጸም በመሆኑ፣ የአካባቢውን ነዋሪዎች ደኅንነት ሙሉ በሙሉ ማረጋገጥ እንዳልታቻለ ገልጸው ነበር፡፡

በመሆኑም የዜጎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ ጥቃት የደረሰባቸው ነዋሪዎች ራሳቸውን እንዲከላከሉ፣ መንግሥት አሠልጥኖ ጦር መሣሪያ የሚያስታጥቃቸው መሆኑንም ጠቁመው ነበር፡፡ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ መለስ በየነ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የማስታጠቁ ሥራ በዚህ ሳምንት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሠረት በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ከተመረጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለተወጣጡ 1,282 ነዋሪዎች የሦስት ቀናት የሚሊሻ ሥልጠና በመስጠት የጦር መሣሪያ እንዲታጠቁ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር በተያዘው ዕቅድ መሠረት እንዲታጠቁ የተወሰነው 3,560 ነዋሪዎች መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡ በዚህም መሠረት የተቀሩት ነዋሪዎች በመከላከያ ሠራዊቱና በክልሉ የፖሊስ ኃይል አማካይነት ሥልጠና እያገኙ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በተለያዩ ኃይሎች የተደራጁ ታጣቂዎች ጥቃቱን እየሰነዘሩ መሆኑን የገለጹት አቶ መለስ በየነ፣ በዋናነት ግን ‹‹የጉምዝ ኃይል›› ብሎ ራሱን የሚጠራው የታጠቀ የፖለቲካ ኃይልና የኦነግ ሸኔ አማፂ ቡድን መሆናቸውንና ከውጭ ባሉ ሌሎች ኃይሎች ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ጠቁመዋል፡፡

ከዓመት በፊትም ይኸው ኃይል በታላቁ የህዳሴ ግድብ ውኃ የሚያርፍበት አካባቢም ላይ ይደረግ የነበረውን ምንጣሮ ለማስተጓጎል ሙከራ አድርጎ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ (ዮሐንስ አንበርብር ~ ሪፖርተር)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top