Connect with us

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት መግለጫ

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት መግለጫ:-
Photo: Social Media

ፓለቲካ

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት መግለጫ

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት መግለጫ:-

 ~ ጦርነት ጎሳሚ ያላቸውን አንዳንድ የአማራ ክልል አመራሮችን ወቀሰ፣

~ “መተከል የእኛ ነው” የሚለው የተዛባ ትርክት ነው፣

(ሙሉ መግለጫው እነሆ)

“የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህገ-መንግሥት የሚፈርሰው የፌዴራል ስርዓቱ እንዲፈርስ ቅዥት የሚመኙ አካላት ሲሳካላቸው ብቻ ነው፡”

የኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት እና የፌዴራል ስርዓቱ ባሳለፍናቸው 27 አመታት በክልሉ የሚኖሩ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ህገ-መንግሥቱ ያጎናጽፋቸውን ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ-መንግስተዊ መብታቸውን ተጠቅመው በፓለቲካው፣  በፍትህ፣ በማህበራዊ እና  በኢኮኖሚው ዘርፍ በተጨባጭ ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸውን ተረጋግጧል።

ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በክልሉ በአንዳንድ ቦታዎች አገራዊ ለውጡ ያልቸመቻቸው በጥቂት ቡድኖችና የግል የፓለቲካ ፍላጎት ባላቸው ፀረ-ሠላም ተልዕኮ ያነገቡ አካላት  በሚፈጠረው  የፀጥታ ችግር  በአጎራባች የአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በኩል በተደጋጋሚ  በመንግስት ሚዲያዎችን ጭምር በመጠቀም የክልሉን ነባራዊ እውነታና ተጨባጭ ሃቁን ባላገናዘበ መልኩ  በክልሉ አልፎ- አልፎ የሚከሰቱ  የፀጥታ ችግሮች የክልሉ ህገ-መንግሥት አግላይና በክልሉ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን ያገለለ በመሆኑንና በክልሉ ተመጣጣኝ ውክልና ባለመኖሩ ነው በማለት በሚዲያ ሲያስተጋቡ ይስተዋላል።

በሌላ በኩል የክልሉን ህገ-መንግሥት የማሻሻል ስልጣንና  ሃላፊነት ክልሉን የመሰረቱት አምስቱ የነባር ብሄረሰቦች የበርታ፣ የጉሙዝ፣ የሽናሻ፣ የማኦና ኮሞ እና እንዲሁም በክልሉ ለዘመናት አብረው የሚኖሩ  ህዝቦች እንጂ የጥቂት የፓለቲካ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች እንዳልሆነ ጠንቅቆ መረዳት ያስፈልጋል።

ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ጊዜያት በአንዳንድ ግለሰቦችና የፓለቲካ ፍላጎት  ባላቸው  አካላት በማህበራዊ ሚዲያ አንድን በህገ-መንግስቱ የተዋቀረን ክልልና ዞንን “መተከል የኛ ነው ” በሚል የተዛባና ፈጽሞ ሊሆን በማይችል ትርክት ሲያስተጋቡ ይውላሉ።

“መተከል የእኛ ነው” የሚለው የተዛባ ትርክት  ምንዓልባትም እውን የሚሆንላቸው የኢትዮጵያ ብሄሮችን፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በጋራ ፈቅደውና አምነው ያጸደቁት የጋራ ቃል-ኪዳን የሆነው የፌዴራላዊ ስርዓትና ህገ-መንግሥቱ ሲፈርስላቸው ብቻ  መሆኑን በውል ሊገነዘቡት ይገባል።

ከዚህ ባሻገር የክልሉ መንግሥት በዞኑ በአንዳንድ አከባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት የክልሉንና የፌደራል የፀጥታ አካላትን በማስተባበርና በማቀናጀት በቀጠናው  አስተማማኝና ዘላቂ ሠላም ለማስፈን የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሌት ተቀን ችግሩን ለመፈታት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ይህ ባለበት ሁኔታ እንደከዚህ ቀደሙት ሁሉ ከክልሉ መንግሥት ጎን በመሆን የፀረ-ሠላም ተልዕኮ ያላቸውን እኩይ ተግባር በማክሽፍ የተጀመረው የብልጽግና ጉዞን ከማሳለጥ ውጪ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በተለይም በከፍተኛ አመራሩ በኩል በየጊዜው በሚዲያ የሚደረገው ዘመቻና የጦርነት ነጋሪት መጎሰም በየትኛውም መስፈርትና መመዘኛ ተቀባይነትና አግባብነት የሌለው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

“የተጋረጠብንን ጊዚያዊ ፈተናዎችን በጋራ በመሻገር የክልላችን ህዝቦች አንድነትንና አብሮነት በማጠናከር አገራዊ ብልጽግናን እውን እናደርጋለን”፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት

ጥቅምት 08/2013 ዓ.ም

አሶሳ፣

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top