Connect with us

“ታላላቅ ህዝባዊ ተሳትፎዎችን በመፍጠር ግድቡ እንዲጠናቀቅ ለመስራት ዝግጁ ነኝ”-ዶ/ር አረጋዊ በርሔ

“ታላላቅ ህዝባዊ ተሳትፎዎችን በመፍጠር ግድቡ እንዲጠናቀቅ ለመስራት ዝግጁ ነኝ”-ዶ/ር አረጋዊ በርሔ
የኢትዬጵያ ፕሬስ ድርጅት

ዜና

“ታላላቅ ህዝባዊ ተሳትፎዎችን በመፍጠር ግድቡ እንዲጠናቀቅ ለመስራት ዝግጁ ነኝ”-ዶ/ር አረጋዊ በርሔ

“ታላላቅ ህዝባዊ ተሳትፎዎችን በመፍጠር ግድቡ እንዲጠናቀቅ ለመስራት ዝግጁ ነኝ”-ዶ/ር አረጋዊ በርሔ
ሙሐመድ ሁሴን

ግድቡ የእናቶችን ችግር የሚቀርፍ በመሆኑ ታላቅ ህዝባዊ ተሳትፎዎች ለመፍጠርና ግድቡን ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን ዶ/ር አረጋዊ አስታወቁ፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ወደ ሹመት መምጣታቸው ትልቅ አገራዊ ለውጥ ነው ብለዋል፡፡

ዶ/ር አረጋዊ በርሔ በትናንትናው ዕለት ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው በመሾማቸው ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው፤ብዙ አስተዋጽኦ ሊያደርጉበት የሚችሉት ስራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ከህዝብ ጋር ብዙ የሰሩ በመሆናቸው ማህበረሰቡን በማስተባበርና ተግባሩን ዳር በማድረስ በኩልም የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

ኃላፊነቱ ከባድና ለአገር ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ከመሆኑም ባለፈ አንድነትን በማጠናከርና ኢኮኖሚን በመለወጥ በኩል ከፍተኛ ሚና የሚያበረክት ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸው፤የተቻለኝን ያህል አስተዋጽኦ የማደርግበት ቦታ ላይ በመመደቤ ደስተኛ ነኝ ብለዋል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ያሉበትን ችግሮች በመቅረፍና ታላቅ ህዝባዊ ተሳትፎዎች እንዲኖሩ በማድረግ በቁርጠኝነት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

በህዳሴው ግድብ ላይ ህዝባዊ ንቅናቄው የላቀ ተሳትፎ እንዲኖረው ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ባሳተፈ መልኩ የተለያዩ ሥራዎችን ለመስራት ዕቅድ እንዳላቸውም ጠቁመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ወደ ሹመት መምጣታቸው ትልቅ አገራዊ ለውጥ መሆኑንም ዶ/ር አረጋዊ ተናግረዋል።

ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች አሁን ላይ ወደ ሹመት እየመጡ ያለበት መንገድ በአወንታዊ ሊታይ የሚችል ነው ያሉት ዶክተር አረጋዊ፤ አሁን ላይ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ሁሉም ባለው ችሎታ እየተመዘነ ሀገሩን ሊያገለግል የሚችልበት እድል መስጠቱ የለውጡ አንድ በጎ መገለጫ ነው ብለዋል፡፡

መንግስት ከዚህ በፊትም ለፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተርነት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን መሾሙ ይታወሳል።

አዲስ ዘመን ጥቅምት 6/2013

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top