Connect with us

ዓቃቤ ሕግ ሃብታቸውን ላላስመዘገቡ ሚ/ዴኤታዎችና የከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት ማስጠንቀቂያ ፃፈ

ሀብትና ንብረታቸውን ያላስመዘገቡ 100 የፌዴራልና የአ.አ ከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ስም ዝርዝር ለፌዴራል ፖሊስ ሊተላለፍ ነው
ታምሩ ፅጌ ~ ሪፖርተር

ህግና ስርዓት

ዓቃቤ ሕግ ሃብታቸውን ላላስመዘገቡ ሚ/ዴኤታዎችና የከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት ማስጠንቀቂያ ፃፈ

የፌደራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን የፌደራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት ባለስልጣናት ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ አዋጁን መሠረት አድርጎ በተለያየ ጊዜ ያቀረበውን ጥሪ ከቁብ ያልቆጠሩ አሥር ሚኒስትር ዴኤታዎችና በርካታ የከተማ አስተዳደሩ ባለስልጣናት ከቅጣት ጋር ሃብታቸውን ባጭር ጊዜ እንዲያስመዘግቡ  የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማስጠንቀቂያ ፃፈ።

ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጌዴዮን ጢሞቴዎት ዛሬ ከአንድ ሰዓትበፊት በሰጠት የሦስት ወራት የመስራቤታቸው የሥራ አፈፃጸም ሪፖርት ላይ እንዳብራሩት፣ ኮሚሽኑ ሃብታቸውን ያላስመዘገቡ ባለስልጣናትን ሥም ዝርዝር አሳውቋል። ተቋማቸውም አዋጁን መሰረት አድርጎ ከቅጣት ጋር ባጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያስመዘግቡ ደብዳቤ ጽፎላቸዋል። የማያስመዘግቡ ከሆነ ሕጉን ጠብቀው ሕግ የማስከበር ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ዓቃቤ ሕግ አደረጃጀቱን በማሻሻል ሦስት የነበሩትን የምክትል ጠቅላይ ዓቃቤያነ ሕግ ወደ አራት ከፍ በማድረግ አሰራሩን ማጠናከሩን ጠቁመው አዳዲስ ዳይሬክቶሬቶች መደራጀታቸውን ገልጸዋል። ዓቃቤ ሕግ በወንጀል ክስመስርቶባቸው በክርክር ከተረቱ ፍርደኞች 412 ሚሊዮን ብር በድርድር እንዲመልሱ መደረጉን ጌዴዮን(ዶ/ር) ተናግረዋል።

የዋስትና መብት ቢከበርላቸውም ሊለቀቁ ስላልቻሉት የኢዴፓ አመራር አቶ ልደቱ አያሌው የተጠየቁት ዋና ዓቃቤ ሕጉ፣ የሳቸው ጉዳይ በክልል የተያዘ በመሆኑ ማብራሪያ መስጠት የሚችለው ክልሉ መሆኑን ጠቁመዋል።(ታምሩ ፅጌ ~ ሪፖርተር

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top