Connect with us

በአቶ ልደቱ ጉዳይ ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳያከብር ቀረ

በአቶ ልደቱ ጉዳይ ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳያከብር ቀረ
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

በአቶ ልደቱ ጉዳይ ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳያከብር ቀረ

በአቶ ልደቱ ጉዳይ ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳያከብር ቀረ

~ “ፖሊስ እየጣሰ ያለው ህገመንግስቱን ነው” ዳኞች

አቶ ልደቱ አያሌው በዛሬው እለት የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ፍርድ ቤቱ በዛሬው እለት ሁለት ጉዳዮችን ለማየት ነበር ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው። የመጀመሪያው የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሁለት ግዜ የተላለፈውን የአቶ ልደቱን ልቀቁ ትእዛዝ ባለማክበሩ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በኩል ትእዛዙ እንዲደርሳቸው እና አቶ ልደቱ እንዲለቀቁ፣ የማይለቁም ከሆነ ምክንያታቸውን ቀርበው እንዲያስረዱ፣ ሁለተኛ በተጠረጠሩበት ህገ ወጥ ሽጉጥ የአቃቢ ህግ ምስክሮችን ለማድመጥ ነበር።

በመጀመሪያው ጉዳይ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንም ሆነ ከቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በችሎት ተገኝቶ መልስ የሰጠ የለም።

በዚህ ግዜ አቶ ልደቱ ይሄ ችሎት ለከሳሽም ሆነ ለተከሳሽ እኩል መብት ነው የሚሰጠው። በዚህ ረገድ ፍረድ ቤቱ በፖሊስ ላይ እያሳየ ያለው ትግስት ተገቢ አይደለም። በዚህ ሁኔታስ  ከዚህ ችሎት ፍትህ አገኛለሁ ብዬ እንዴት አስባለሁ?!  አሁን ለፖሊስ ያሳየውን ትእግስት በተራው ዜጋ ላይ ወይንም በእኔ ላይ ያደርገዋል ወይ?!” የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል።

ዳኞችም “እኛ ያለን አቅም ውሳኔያችን ተፈፃሚ እንዲሆን  ማዘዝ ነው። ይህንን ትእዛዝ የሚያስፈፅም ጦር ሰራዊት የለንም። ጦር ሰራዊት ቢኖረን አዘን እናስፈታህ ነበር። ፖሊስ እየጣሰ ያለው ህገ መንግስቱን ነው። ተቋሙ እየናቀ ያለው የእኛን ተቋም ሳይሆን የራሱን ተቋም ነው” ብለዋል።

ጠበቃ አሸናፊ ተስፋዬም የእናንተ እስኪሪብቶ ከጦር በላይ ነው ማዘዝም ትችላላችሁ በማለት መልስ ሰጥተዋል።

በመጨረሻ ችሎቱ የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ እና ወንጀል መከላከል ቢሮ ሃላፊውን ለምን በተደጋጋሚ ከፍርድ ቤት የሚሰጥን ትእዛዝ እንደማያከብሩ ቀርበው እንዲያስረዱ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ደግሞ አቶ ልደቱን በአስቸኳይ እንዲፈታ ወስኗል። 

ትእዛዙንም አቶ ልደቱን አጅቦ የሚመጣው ሳጅን መሀመድ አሊ የሚባለው የፖሊስ ባልደረባ እንዲያደርስ ከችሎት ታዟል። 

በመጨረሻም በ9/2/13 ከጠዋቱ 4 ሰአት ቀጠሮ ሰጥቷል። 

አሁንስ የበላይ የሆነው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በአደራ ከማን ተቀበልኩ ይል ይሆን?(ምንጭ አዳነ ታደሰ)

 

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top