Connect with us

የኮንደሚኒየም የባንክ ዕዳ መክፈል የተሳናቸው አካል ጉዳተኛዋ ሙሉ ክፍያ ተከፈለላቸው !!

የኮንደሚኒየም የባንክ ዕዳ መክፈል የተሳናቸው አካል ጉዳተኛዋ ሙሉ ክፍያ ተከፈለላቸው !!
Photo: Straff reporter

ማህበራዊ

የኮንደሚኒየም የባንክ ዕዳ መክፈል የተሳናቸው አካል ጉዳተኛዋ ሙሉ ክፍያ ተከፈለላቸው !!

“እናመሰግናለን!!”
—***—
የኮንደሚኒየም የባንክ ዕዳ መክፈል የተሳናቸው አካል ጉዳተኛዋ ሙሉ ክፍያ ተከፈለላቸው !!
(ዘ ኮረም ክብረት)
—————-
ወ/ሮ አታሌ አስፋው የተባሉ አካል ጉዳተኛ ሴት በቦሌ አራብሳ በተባለ ቦታ አስር ዘጠና ኮንደሚኒየም ቢደርሳቸውም ለባንክ በየወሩ 760 ብር የባንክ ዕዳ ለመክፈል ባለመቻላቸው ‹‹ብሩን ካልከፈልኩ ቤቱ ውስጥ ለመኖር አልችልም፡፡ ሰማዩ ተደፍቶብኝ በጭንቅ ውስጥ ላይ ነኝ፡፡ ጎዳና ከመውደቄ በፊት ችግሬን ተረድታችሁ አስፈላጊ ከሆነም ቤቴ ድረስ በመምጣት የችግሬ ተካፋይ በመሆን ከጎዳና ህይወት ታደጉኝ፣ ጎዳና ብወድቅም የእናንተ ሸክም ከመሆን አልድንም ፣ በኢትዮጵያ አምላክ ተጨንቅያለሁ፣ ተኝቼ እንቅልፍ የለኝም፣ ሰማዩ ተደፍቶብኛል፡፡ ሲሉ የድጋፍ ጥሪ ማቅረባቸው ከዚህ ቀደም ‹‹አካል ጉዳተኛዋ የኮንደሚኒየም የባንክ ዕዳ መክፈል ተስኗቸዋል በሚል.›› ርእስ በድሬቲዩብ ማስነበባችን ይታወሳል፡፡ እኝህ ሴት ታድያ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ መኖርያ ቤታቸው ሄደን አነጋግረናቸዋል፡፡

ወ/ሮ አታሌ በፈገግታ ነው የተቀበሉን፡፡ ‹‹ምን አዲስ ነገር አለ ብለን ጠየቅናቸው፡፡ ›› ‹‹በጣም ሲያስጨንቀኝ የነበረው ሸክም ተቃሎልኛል ፣ የቤቴ ቀሪ ሙሉ ክፍያ ተከፍሎልኛል፡፡ በመጀመርያ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ!! በመቀጠል ቤቱ ከደረሰኝ ጀምሮ ያልተለየኝ ተስፋዬ ገብረማርያም፣ ተፈሪ እንዲሁም እከሌ እከሌ ብዬ ስማቸውን ዘርዝሬ መጥራት የማልችላቸው በአገር ውስጥ ሆነ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በሀሳብ፣ በገንዘብ፣ በአካል ቤቴ ድረስ በመገኘት አጋርነታቸውን ላሳዩኝ፣ ስማቸውን ሳይጠቅሱ በባንክ ቁጥሬ የቻሉትን ያስገቡልኝ በሙሉ የጨለመው ህይወቴ አንሰራርቶ እንዲቀጥል ላደረጉልኝ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በሄዱበት ሰላም ስኬት እድሜ እና ጤና እንዲገጥማቸው ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ እኔ ያደረጉልኝ በቃላት ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል፡፡ ለህዝብ በማድረስ ድሬቲዩብ፣ ዘ-ኮረም ክብረት፣ ፍሬው አበበ፣ ተስፋዬ ገብረማርያም በድጋሚ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
አሁን ላይ ጭንቀቴ ተወግዷል፡፡ የቤቱን ባለይዞታነት ማረጋገጫ ካርታ ተሰጥቶኛል፡፡>>ሲሉ ነው በደስታ ስሜት ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡

ወ/ሮ አታሌ አስፋው የሰማ ሰው ሁሉ አልቅሶ አቅሙ የቻለውን አድርጎልኛል እኔ ቃል የለኝም፡፡ እኔ ሳስበው የነበረው ቤቱን ባለመክፈሌ ቤቱ ታሽጎ እኔም ጎዳና እወጣ ነበር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ደርሶልኛል ከልብ አመሰግናለሁ!! በተለይ በተለይ በአሜሪካን አገር የሚገኝ ሳሚ ከነባለቤቱ እንዲሁም ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቹን አስደውሎ የቀረውን ክፍያ ሙሉውን እንዲከፈል አድርጎልኛል፡፡ ከዛ በፊትም ቢሆን በተለያየ ጊዜ በባንክ ቁጥሬ የቻሉትን ገንዘብ ከረዱኝ መካከል እዮብ የተባለ ሰው 20 ሺህ ብር፣ስማችን ፈጣሪ ያውቀዋል ብለው የረዱኝ ኢትዮጵያዊያን፣ በሀሳብ ያጽናኑኝ ቤቴ ድረስ በመምጣት አይዞሽ ያሉኝ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ እዚህ ላይ ስማቸውን ያልጠቀሱኳቸው ብዙ ናቸው፡፡

ንጽጽር ቤቱ ከመከፈሉ በፊትና በኋላ

‹‹አሁን ያለጭንቀት እንደልቤ እተኛለሁ፣በማመልከበት ቦታ ካለ ሀሳብ እሄዳለሁ፣ ደስታዬ ወደር የለውም፡፡ አሁን ኮ ቤቱ የኔ መሆኑን አረጋግጫለሁ፣ ካርታው በእጄ ላይ ነው፡፡ ቤቴ ተሟልቷል፤ ልብሴ በፌስታል ነበር የማስቀምጠው አሁን ተቀይሯል፡፡ ከዚህ ቀደም ቤቴ ውስጥ መቀመጫ አልነበረኝም አሁን ግን ሶፋ ተገዝቶልኛል፡፡ ይሄ ጎድሎብኛል የምለው ነገር የለኝም፡፡>> ሲሉ ወ/ሮ አታሌ አስፋው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

#ከአዘጋጁ :- በድሬቲዩብ ላይ የወ/ሮ አታሌ ችግር በማንበብ በአገር ውስጥም ከውጭም ድጋፍ ያደረጋችሁ ወገኖቻችን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን!! ፈጣሪ ብድሩን ይከፍላችሁ ዘንድ ፀሎታችን ነው።

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top