Connect with us

“ማህበራዊ ድረ-ገጽን በአግባቡ አለመጠቀም የህግ ተጠያቂነትን ያስከትላል” ጠ/ዐ/ሕግ

"ማህበራዊ ድረ-ገጽን በአግባቡ አለመጠቀም የህግ ተጠያቂነትን ያስከትላል" ጠ/ዐ/ሕግ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

ህግና ስርዓት

“ማህበራዊ ድረ-ገጽን በአግባቡ አለመጠቀም የህግ ተጠያቂነትን ያስከትላል” ጠ/ዐ/ሕግ

“ማህበራዊ ድረ-ገጽን በአግባቡ አለመጠቀም የህግ ተጠያቂነትን ያስከትላል” ጠ/ዐ/ሕግ

በሀገራችን ከማህበራዊ ድረ-ገጽ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ የሰውዘር አበበ ገልጸዋል፡፡

የማህበራዊ ድረ-ገጽ አጠቃቀምን በማዘመንና በህግ በተቀመጠው አግባብ በመጠቀም እራስን ከተጠያቂነት መከላከል እንደሚገባ የገለጹት ዐቃቤ ህጓ የማህበራዊ ድረ-ገጽ አጠቃቀምን አስመልክቶ በህግ የተቀመጡ ገደቦችን ሳያልፉ ለታለመለት አላማ ብቻ በመጠቀም ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ 

ነገር ግን የማህበራዊ ድረ-ገጽን ላልተፈለገ እኩይ ተግባር በማዋል የሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ለማስተላለፊያነት በመጠቀም የሌሎችን ሰብዓዊ ክብር የሚነኩ እንዲሁም ባልተጨበጠ መረጃ ህብረተሰቡ ግራ እንዲጋባ ለማድረግ ያለአግባብ በሚጠቀሙ አካላትን ተጠያቂ የሚያደርግ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትና የጥላቻ ንግግርን የሚከለክል አዋጅ ወጥቶ ስራ ላይ እንደዋለ አስታውሰዋል፡፡ 

በአዋጁ ከተካተቱት መካከልም የጥላቻ ንግግርን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ወይንም ሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎችን በመጠቀም ያስተላለፈ እስከ 2 አመት በሚደርስ እስራትና በብር 100 ሺ እንደሚያስቀጣ አብራርተዋል፡፡    

በተጨማሪም በተላለፈው የጥላቻ ንግግር ምክንያት በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት ደርሶ እንደሆነ የቅጣቱ ጊዜ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ሲሆን ሀሰተኛ መረጃዎችን በአደባባይ ስብሰባዎች፣ በብሮድካስት፣ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በምስል፣ በጽሁፍ ወይም በቪዲዮ በመጠቀም ያሰራጨ እንደሆነ 1 ዓመት በሚደርስ እስራት ወይም በ50 ሺ ብር ቅጣት ሊተላለፍበት ይችላል ያሉት ዐቃቤ ህጓ መረጃው ከ5000 በላይ ተከታይ ባለው ማህበራዊ ድረ-ገጽ የተላለፈና ጉዳት የደረሰ እንደሆነ ግን የቅጣት መጠኑ ከ2 እስከ 5 ዓመት ሊደርስ ይችላል ብለዋል፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top