Connect with us

“ስፖርት እና ሌላ ነገር መለያየት አለበት” – አትሌት ደራርቱ 

"ስፖርት እና ሌላ ነገር መለያየት አለበት" - አትሌት ደራርቱ
ኢትዮጵያ_ቼክ

ስፖርት

“ስፖርት እና ሌላ ነገር መለያየት አለበት” – አትሌት ደራርቱ 

“ስፖርት እና ሌላ ነገር መለያየት አለበት” – አትሌት ደራርቱ 

አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለትላንቱ ውድድር ወደ ስፔን (ቫሌንሺያ) ስታመራ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ያጋጠማት ምንድን ነው ?

አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ መጉላላት እንደደረሰባት እና የኢትዮጵያ አሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ ኤርፖርት በመገኘት ችግሩ እንዲቀረፍ እንዳደረገች ከምስጋና ጋር ገልፃለች።

አትሌት ደራርቱ ስለተከሰተው ችግር ለኢትዮጵያ ቼክ ተከታዩን ብላለች ፦

“ባለፈው እሁድ ምሽት አትሌት ለተሰንበትና ማናጀሯ ሀይሌ ኤርፖርት ሆነው ‘እንዳንሄድ ታግደናል’ ብለው ስልክ ደወሉልኝ። ያላሟሉት ዶክመንት እንዳለ ስጠይቃቸው ሁሉም እንዳላቸው ነገሩኝ፣ ከዛም ወደ ኤርፖርት ሄድኩ።

አለመግባባቱ የነበረው ከጤና ሚኒስቴር በተፃፈ ደብዳቤ ዙርያ ነበር። አትሌቷ ደብዳቤውን ይዛ ነበር፣ አሳይቻለሁ አለች፣ ኤርፖርት ያሉት ደግሞ አላሳየችንም ይሉ ነበር።

ጉዳዩ ትልቅ አልነበረም፣ ዋናው እንኳን ተሳካላት። እኔ ልናገር የምፈልገው ስፖርት እና ሌላ ነገር መለያየት አለበት፣ ሁለቱ ቢለያይ ጥሩ ይመስለኛል። አሁን አትሌት ለተሰንበት ወደ ሀገር ትመለሳለች፣ ያኔ ይቅርታ መጠየቅ ያለበት አካል ካለ ይቅርታ ይጠይቃል።”

ምንጭ- ኢትዮጵያ_ቼክ

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top