Connect with us

መረጃ አዘል ጥያቄ

መረጃ አዘል ጥያቄ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

መረጃ አዘል ጥያቄ

ህወሓት “በሕገመንግስቱ መሰረት የፌዴራል የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ስልጣኑ ያበቃል፡፡ ስለሆነም ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ አሁን  ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር እና ም/ጠ/ሚኒስትር የቀድሞ ተብለው ነው የሚጠሩት።…ከእንግዲህ ከፌደራል መንግስት ጋር የሚያገናኘን አንድም ፖለቲካዊ ሆነ ህጋዊ ግንኙነት የለንም፤ ከቢሮክራሲ ስራዎች ውጪ” በማለት በህወሓት የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባሉ አቶ ጌታቸው ረዳ በኩል በመገናኛ ብዙሃን አቋሙን ይፋ አድርጓል፡፡

ይኸንን ተከትሎም በተለያዩ የፌደራል መንግሥት የፖለቲካ ሹመት ቦታ ላይ የነበሩ አባላቱን፣ የክልሉ ተወካይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ኃላፊነታቸውን በመልቀቅ ለህወሓት ሪፖርት እንዲያደርጉ አዟል፡፡

የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክርቤት በበኩሉ  ነሃሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ጉባዔ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ እንዳልተደረገ፣ እንዳልተፈጸመ እና እንደማይጸና ውሳኔ ማስተላለፉን የሚታወስ ነው፡፡ ይህ የምክርቤቱ ውሳኔ በህወሓት በኩል ባለመከበሩም በትላንትናው ዕለት አዲስ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚህ መሰረት  የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ብሏል፡፡

ጥያቄ

ይኸ በፌዴራል መንግስት እና በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኩል የተፈጠረው አለመግባባት እንዴት ያዩታል? ሁለቱ ወገኖች የያዙት አቋም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ከማስገኘት አኳያ ያለው ፋይዳ ምንድነው ይላሉ? (ጨዋነት የጎደላቸው አስተያየቶችን አናስተናግድም)

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top