Connect with us

ፍርድ ቤቱ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ለተከሰሱ አራት ግለሰቦች የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው አዘዘ

ፍርድ ቤቱ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ለተከሰሱ አራት ግለሰቦች የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው አዘዘ
በድሬቲዩብ ሪፖርተር

ህግና ስርዓት

ፍርድ ቤቱ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ለተከሰሱ አራት ግለሰቦች የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው አዘዘ

ፍርድ ቤቱ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ለተከሰሱት 4 ግለሰቦች የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው አዘዘ፡፡

ተከሳሾቹ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በቀጠሮዋቸው መሰረት ዛሬ ክሱ ተነቦላቸዋል፡፡

ተከሳሾቹም አንደኛ ጥላሁን ያሚ ባልቻ፣ ሁለተኛ ከበደ ገመቹ መገርሳ፣ ሶስተኛ አብዲ አለማሁ እና አራተኛ ላምሮት ከማል መሃመድ ናቸው፡፡

ተከሳሾች ለዛሬ ከባለሙያ ጋር ተማክረው ክሱን ለማንበብ በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያሉት ተከሳሾች ጠበቃ የማቆም አቅም እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም 4ኛ ተከሳሽ የሆነችው ላምሮት ከማል ጠበቃ የማቆም አቅም እንዳላት ገልጻ ሆኖም የሚቆምልኝ ጠበቃ አጥቻለሁ በማለት ለፍርድ ቤቱ አስረድታለች፡፡

ይህንንም ተከትሎ ፍርድ ቤቱ የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ተከሳሾቹ በተነበበላቸው ክስ ላይ መቃወሚያ ካላቸው ለመመልከት ለጥቅምት 4 ቀን 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ፋና ዘግቧል፡፡

ተከሳሾቹ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1 ሀ እና ለ እንዲሁም የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1 ሺህ 176/2012 አንቀፅ 3/2 የተደነገገውን በመተላለፍ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ ተጠርጥረው መከሰሳቸው የሚታወስ ነው፡፡(ኢዜአ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top