Connect with us

ሌላው ቀርቶ ዶክተር አብይም መንግስት የለም ብትል አንሰማህም ትመራናለህ

ሌላው ቀርቶ ዶክተር አብይም መንግስት የለም ብትል አንሰማህም ትመራናለህ፤ ትመራናለህ፡፡ከፍቅሩ ምስጋናው
AP Photo/Francisco Seco, file

ነፃ ሃሳብ

ሌላው ቀርቶ ዶክተር አብይም መንግስት የለም ብትል አንሰማህም ትመራናለህ

ሌላው ቀርቶ ዶክተር አብይም መንግስት የለም ብትል አንሰማህም ትመራናለህ፤ ትመራናለህ

(ከፍቅሩ ምስጋናው)

እዚሁ ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ አንድ ሰው ልዩ የሆነችና የገረመቺኝን አባባል ፖስታ አድርጎ አየሁት፡፡ ሰውዬው አይደለም ህወሃት አንተ ራሱ ይልና ጠቅላይ ሚኒስትሩን “ዶክተር አብይ ራሱ መንግስት የለም ብትል አንቀበልህም፤ ትመራናለህ ትመራናለህ፡፡” ይላል፡፡

አባባሉ ቀላል ይመስላል ግን መራር እውነት ነው፡፡ ዶክተር አብይን ደግፈን ሜዳ ላይ ወጥተናል፡፡ ሚሊዮኖች ሲሰደዱ ዝም ያልነው ብርሃን ይሆናል እንደተባለውም እንሻገራለን ብለን ነው፡፡ እዚህም እዚያም ሰውን ያክል ፍጥረት ሲታረድ የመሻገር መስዋዕት እንደ ቀረበ ቆጥረን አቀርቅረን ያለፍነው ለለውጥ ዋጋ ለመክፈል ነው፡፡ ለዚህ ነው እንኳን ህወሃት አብይም እዳችንን ሳይመልስ ያሰብንበት ሳንደርስ በቃኝ ቢል አይበቃህም የምንለው፤

እርግጥ ነው የለውጥ ሃይሉ ብዙ ችግር አለበት፡፡ አንዱ የለውጥ ሃይሉ ችግር የመቀሌውን ቡድን እያባባለ ኪሱ አብጦ ደረቱ ገልብጦ ከመሸሽ መልሶ አዲስ አበባ እስከ መምጣት እንዲቋምጥ አድርጎታል፡፡

ህወሃት ጨርቋን ሳትሰበስብ ወደ መቀሌ ስትፈረጥጥ ያኔ ከቂሊንጦ መዳን ነበር ምኞቷ ውላ አድራ ግን እነ ጃዋርን ከቂሊንጦ ስለማስፈታት አሰበች፡፡ ይህንን ህግ አስከብሮ አደብ የማስገዛት ስራ የዶክተር አብይ መንግስት ቢሆንም ሲሽኮረመም ቆይቷል፡፡ ህዝብና አብይ ቢቀያየሙ አብይ ህወሃትን ባለመቅጣቱ እንጂ ህዝብ ህወሃትን በመስማቱ እንዳልሆነ ህወሃትም ታውቀዋለች፡፡

መስከረም ሃያ ስድስት ሆኗል፡፡ የአቶ ጌታቸው አሰፋ ፉከራ ብዙ ነበር እንደ እሳቸው አባባል መስከረም ሃያ ስድስት እሳቸው አዲስ አበባ በገቡ ድጋሚ ግንቦት ሃያ ባሉ ግን አልሆነም፡፡ ህወሃት በምክር ቤት ወሰንኩ ስትል ሌላው ክልል በምክር ቤት የመወሰን መብት እንደሌለው ማሰቧና መክራ ልታወላግድ መሞከሯ ወልጋዳ ፖለቲካ እንዳሰመጣት ማሳያው ነው፡፡

እኛ የተሻለ ነገን እንመኛለን፤ የተሻለ ነገን የሚሰብከን ያልተሻለ ሃያ አምስት አመት ያሰቃየን የሀገር ጠላት አይደለም፡፡ ይህ ህወሃትን እንኳን መወከል የማይችል ቡድን የትም እንደማይደርስ እያወቀ ለሀገር ለዲሞክራሲና ለነጻነት ዋጋ የከፈለውን የትግራይ ህዝብ ጥቅም ጥቅሙ ስለተነካበት ብቻ በማኩረፉ እንዳይጠበቅ ማድረጉ የሚያሳዝን ነው፡፡ ያም ቢሆን የእኛ አቋም እንኳን ጌታቸው ረዳ በቃ ሲል ልንሰማ ዶክተር አብይም በቃኝ ቢል የጀመርከውን ጨርስ እንላለን እንጂ አንቀበልም፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top