Connect with us

የ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ከቀኑ በ6:00 ሰዓት ይፈፀማል

የ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ከቀኑ በ6:00 ሰዓት ይፈፀማል
በድሬቲዩብ ሪፖርተር

ዜና

የ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ከቀኑ በ6:00 ሰዓት ይፈፀማል

የታዋቂው የአደባባይ ምሁር የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አባት የፕሮፌሰር መስፍን የዜና እረፍታቸው ከተሰማ ጀምሮ ክብራቸውን የሚመጥን የቀብር ስነ-ሥርዓት ለማካሄድ የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴ ተዋቅሮ በስራ ላይ ይገኛል።

የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴው ባወጣው የጊዜ ሌዳ መሠረት የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም የቀብር ስነ-ሥርዓት የሚፈፀመው ነገ ማክሰኞ ማለትም መስከረም 26 ቀን  2013 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሲሆን ከቀብር ስነ-ሥርዓቱ በፊት ከጥዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 5:00 ሰዓት ድረስ በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ልደታ አዳራሽ ውስጥ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሽኝት ዝግጅት ይደረጋል።

በመቀጠልም ከ ቀኑ 5:30 ላይ አስከሬናቸው በወዳጅ ዘመዶቻቸው እና በአፍቃሪዎቻቸው ታጅቦ በልዩ ስነ-ሥርዓት ቀብራቸው ወደ ሚፈጸምበት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ጉዞ ይደረጋል። 

ከቀኑ 6:30 እስከ 7:30 ባለው ጊዜ ስርዓተ-ቀብራቸው የሚፈጸም ይሆናል።(ምንጭ:- ኢሰመጉ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top