Connect with us

ህወሓት በመንግሥት ሹመት ላይ ያሉ አባላቱ ቦታቸውን እንዲለቁ ማዘዙን ገለጸ

ህወሓት በመንግሥት ሹመት ላይ ያሉ አባላቱ ቦታቸውን እንዲለቁ ማዘዙን ገለጸ
በድሬቲዩብ ሪፖርተር

ህግና ስርዓት

ህወሓት በመንግሥት ሹመት ላይ ያሉ አባላቱ ቦታቸውን እንዲለቁ ማዘዙን ገለጸ

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በተለያዩ የፌደራል መንግሥት የፖለቲካ ሹመት ቦታ ላይ የነበሩ አባላቱን፣ የክልሉ ተወካይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ኃላፊነታቸውን ለቀው እንዲወጡ ማዘዙን አቶ ጌታቸው ረዳ ለቢቢሲ ተናገሩ።

አቶ ጌታቸው ረዳ የፓርላማው የስልጣን ዘመን በትናንትናው ዕለት ማክተሙን በመግለጽ፣ ከፓርላማው በተጨማሪ ፓርላማው ያቋቋመው መንግሥም፣ ካቢኔም የተመረጡት ለአምስት ዓመት መሆኑን ጠቅሰው የሰልጣን ዘመናቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልፀዋል።

ስለዚህ ዛሬ በሚካሄደው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ትግራይ ክልል ተወካዮቹን እንደማይሳተፉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

“ትግራይ ክልል ተወካዮች ከምክር ቤቱ እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። በፓርላማ ብቻ ሳይሆን በካቢኔ ውስጥ፣ በሌሎች የመንግሥት የፖለቲካ ሹመት ቦታዎች ላይ የነበሩ የህወሓት ተወካዮች እንደዚሁ እንዲወጡ ተደርገዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አምስተኛ የፓርላማ ዘመን ስድስተኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሰኞ መስከረም 25/2013 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ይካሄዳል።

ጉባኤው በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚገኘው የስብስባ አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያው ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሚያደርጉት ንግግር የሁለቱ ምክር ቤቶችን የጋራ ስብሰባ ይከፈታል።

አቶ ጌታቸው “በአሁኑ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ካቢኔያቸው፣ እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ምንም አይነት ሕጋዊ ስልጣን የላቸውም በማለት፤ ከዛሬ ጀምሮ ከእነዚህ አካላት ጋር ምንም አይነት ሕጋዊ ግንኙነት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም” ብለዋል።

የትግራይ ክልል የምርጫ ጊዜያቸው አልቋል በሚል ግንኙነቱን ከእነዚህ አካላት ጋር ቢያቋርጥም እንደ አቶ ጌታቸው ረዳ ከሆነ ከፍትህ ተቋማት፣ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከዲፕሎማቲክ ሚሽን ከሚሰጡ ተቋማት እና በተለያየ ደረጃ የዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግልጋሎት ከሚሰጡ አካላት ጋር እንደሚሰራ ተናግረዋል።

“መንግሥት በትክክለኛው መንገድ ለመመስረት የሚያስችል እድል እስኪገኝ ድረስ ግንኙነታችን ከእነዚህ ጋር ብቻ ይሆናል” በማለት “ፈርሰዋል” ካሏቸው ጋር ያላቸው ግንኙት መቋረጡን አስታውቀዋል።

የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በተፈጠረው የኅብረተሰብ ጤና ስጋት ሳቢያ ባለፈው ዓመት መካሄድ የነበረበት ምርጫ መካሄድ ሳይችል በመቅረቱ ሁለቱ የፌደራል ምክር ቤቶችና በሁሉም ክልሎች ውስጥ ያሉት ምክር ቤቶች ምርጫው እስኪካሄድ በሥራ ላይ እንዲቆዩ መወሰኑ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ የትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽን በማቋቋም በተናጠል ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ በመወሰኑ ከፌደራል መንግሥቱ በተለይም ደግሞ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫው መካሄድ እንደሌለበት ድርጊቱም ሕገወጥና ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ተገልጾ ነበር።

በዚህም ሳቢያ በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መካከል ያለው አለመግባባት እየተባባሰ ሄዶ የክልሉ ገዢ ፓርቲ ህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከመስከረም 25 በኋላ ከማዕከላዊው መንግሥት ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደሚያበቃ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ ከቀናት በፊት ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ይህንኑ በተመለከተ እንደተናገሩት “በእስካሁኑ እንቅስቃሴ ክልሉ ሕገ-መንግሥቱን አደጋ ላይ ጥሏል” ለዚህም እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሕገ መንግሥታዊ መሰረት መኖሩን አመልክተዋል።

ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል የክልሉን ሕግ አውጪና ሕግ አስፈጻሚውን ማገድ የሚያስችል ሕገ መንግሥታዊ አካሄድ አንዱ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎም ለፌደራል መንግሥት ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋምና የፌደራል የፀጥታ አካላት በማሰማራት ሕገ መንግሥቱን አደጋ ላይ የጣለውን ድርጊት መቆጣጠር ሌላኛው መሆኑን አፈጉባኤው ገልጸዋል።(BBC)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top