Connect with us

አቶ ሽመልስ ልክ ናቸው፡፡ ሁሉም ክልል ራሱን ይገንባ፡፡ ኢትዮጵያን ይደግፍ …

አቶ ሽመልስ ልክ ናቸው፡፡ ሁሉም ክልል ራሱን ይገንባ፡፡ ኢትዮጵያን ይደግፍ
Photo: Social Media

ትንታኔ

አቶ ሽመልስ ልክ ናቸው፡፡ ሁሉም ክልል ራሱን ይገንባ፡፡ ኢትዮጵያን ይደግፍ …

አቶ ሽመልስ ልክ ናቸው፡፡ ሁሉም ክልል ራሱን ይገንባ፡፡ ኢትዮጵያን ይደግፍ፡፡ ያኔ አፍሪካን ያረጋጋል፡፡ ክልሉን ያልገነባ ኢትዮጵያን ያፈርሳል፡፡ ኢትዮጵያን የማይደግፍ ዓላማው መጣል ነው፡፡

ከስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ሀሳብ የሁሉም ክልል መሪዎች ቢሆን እንዴት መልካም ነበር? የክልል መሪዎች ድርሻ ለፌዴራል መንግስቱ መላላክ ሳይሆን የየራሳቸውን ክልል መገንባት ነው፡፡ ክልሉን ያልገነባ መሪ ውጤቱ ሀገር ማፍረስና ችግር መፍጠር ነው፡፡ የኢህአዴግ ሥርዓት ሀገር እገነባለሁ እያለ ክልል አፍርሶ ነው የፈረሰው፡፡

ክልል መገንባት ለክልል መሪ ቀዳሚው አጀንዳ ነው፡፡ አንድ የክልል መሪ ሀገር እገነባለሁ እያ ቢመጻደቅ ወሬ ከማውራት ያለፈ እውነቱ ጠብ የሚል ውጤት አያመጣም፡፡ ሀገር ያለው ክልል ነው፡፡ ወረዳ አስተዳዳሪው ስራው ወረዳን ማልማት ነው፡፡ ዞን ላይ የሾምነው ዞን እንዲያለማ እንጂ ክልል እንዲላላክ አይደለም፡፡ በተሾመበት አደራን መወጣት የተሾመበትን ቦታ መገንባት ነው፡፡

አሁን የሀገራችን ችግር አለመገንባት ነው፡፡ ኦሮሚያ ሆ ብሎ በየምክንያቱ ለጥፋት የሚታዘዘው ወጣት የሥራ አጥነት ችግርና ያልተገነባ ክልል የገባበት የኢኮኖሚ ቀውስ ውጤት ነው፡፡ አማራ ክልል ዛሬም መሳሪያ አንግቦ በየምክንያቱ የሚቆጣው ያልተገነባ ክልል ያስቆጨው ወጣት ነው፡፡

ክልሉን የገነባ ሀገሩን ይደግፋል፡፡ የክልሎች ድርሻ ሀገር መደገፍ ነው፡፡ ሀገርን አለመደገፍ ማለት መመሪያ አልቀበልም፤ አንድነትን አልሻም፤ መደማመጥ አልፈልግም ማለት ነው፡፡ ሀገርን መደገፍ ማለት ተያይዞ ለማደግ መስማማት ማለት ነው፡፡ ሀገርን መደገፍ ማለት ሀገር እንዳይወድቅ የድርሻን መጫወት ማለት ነው፡፡

ኢትዮጵያ ጠንካራ ክልሎች ካልገነቧት ክልሎቹ ሀገርን ደግፈው ካላቆሙ ችግሯ ከእሷ አልፎ ምስራቅ አፍሪካን ያዳርሳል፡፡ ምስራቅ አፍሪካን ሰላም ለማድረግ ቀዳሚው ነገር ሀገርን መስራት፣ ክልልን ማልማት፤ ግጭትን መቀነስ ዲሞክራሲን ማስፈን ነው፡፡

አቶ ሺመልስ አብዲሳ ያሉት በዚህ መንፈስ ቢሆንም ባይሆንም ያሉትን ሲያደርጉት ግን ግቡ ይሄ ነው፡፡ ዛሬ የኦሮሚያ ከተሞች ሀብት ቢኖራቸውም አልተገነቡም፡፡ ኦሮሚያ እንደ ሐዋሳ፣ ባህር ዳርና መቀሌ ያሉ ውብ ከተሞች አልተገነቡላትም፤ ያልተገባ ክልል መሪ ክልል እገነባለሁ ቢል ምን ሐጢአት አለው፡፡ የተገነቡ ክልሎች ሀገር አያፈርሱም፡፡ ሀገር የሚያፈርሰው የፈረሰ ክልል ነው፡፡

Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top