Connect with us

ምርጫ ቦርድ፤ የምርጫ ኦኘሬሽን ዝግጅቱን ለጋዜጠኞች አስጎበኘ (በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

ምርጫ ቦርድ፤ የምርጫ ኦኘሬሽን ዝግጅቱን ለጋዜጠኞች አስጎበኘ (በድሬቲዩብ ሪፖርተር)
በድሬቲዩብ ሪፖርተር

ዜና

ምርጫ ቦርድ፤ የምርጫ ኦኘሬሽን ዝግጅቱን ለጋዜጠኞች አስጎበኘ (በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛውን ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ቁሳቁሶች ከ90 ከመቶ በላይ ማሟላቱን በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች ባዘጋጀው ጉብኝት ላይ ገለፀ።

ቦርዱ በአ/አ ኤግዚቢሽን ማዕከል ለድምፅ አሰጣጥ ሒደት፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ቅጥር ግቢ የምዝገባ ሒደትንየሚመለከቱ ቁሳቁሶችን ለጋዜጠኞች በማስጎብኘት ዝርዝርማብራሪያ ሰጥቷል።

በጉብኝቱ ውስጥ ከድምፅ አሰጣጥ ሒደት ጋር የተያያዙ የጥንቃቄና የሚስጥር አጠባበቅ እንዲሁም ዘመናዊ አሰራር ሒደት በቦርዱ የተለያዩ ባለሙያዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በአሁኑ ወቅት በድምፅ መስጫ ወረቀት ህትመት በስተቀር አብዛኛዎቹ ቁሳቁሶች ዝግጁ ሆነዋል። የድምፅ መስጫ ወረቀት የዘገየው እጩ ተወዳዳሪዎችና ምልክቶቻቸው ከታወቀ በሀላ መከናወን ያለበት ስራ ስለሆነ ነው ተብሏል።

በጉብኝቱ ከታዩት ቁሳቁሶች መካከል በአምስት ቋንቋዎች የተዘጋጁ የመራጮች መዝገቦች፣ የደህንነት መጠበቂያ ያለው ለማባዛትና አስመስሎ ማተም የማይቻል የመራጮች መታወቂያ ካርድ፣ለአስፈፃሚዎች የሚውሉ ቁሳቁሶች፣ በግልፅ የሚያሳዩ የድምፅ መስጫ ሳጥኖች፣ የሚስጢር ድምፅ መስጫ መከለያዎች እና የመሳሰሉ ቁሳቁሶች ይገኙበታል።

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የቦርዱ ሰብሳቢ ለጋዜጠኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ቁሳቁሶቹ ከ90 ከመቶ በላይ መሟላቱን የተናገሩ ሲሆን ወ/ት ሶልያና ሽመልስ የቦርዱ የኮምኒኬሽን አማካሪ ቁሳቁሶች ቀደም ሲል ከነበሩ የምርጫ ቁሳቁሶች ስለሚለዩበት ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ ሰጥተዋል።

ለቀጣዩ ምርጫ 50ሺ900 የምርጫ ጣቢያ እና 50 ሚልየን መራጮች እንደሚኖሩ ከቦርዱ የተገኘ መረጃ ጠቁሟል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top