Connect with us

ወጣቱ አረጋዊ፣ ኢትዮጵያዊው ሊቅ፣ የአንድ ትውልድ ምልክቱ፤ ፕሮፌሰር …

ወጣቱ አረጋዊ፣ ኢትዮጵያዊው ሊቅ፣ የአንድ ትውልድ ምልክቱ፤ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፤ ነፍስ ይማር
Photo: Social Media

ባህልና ታሪክ

ወጣቱ አረጋዊ፣ ኢትዮጵያዊው ሊቅ፣ የአንድ ትውልድ ምልክቱ፤ ፕሮፌሰር …

ወጣቱ አረጋዊ፣ ኢትዮጵያዊው ሊቅ፣ የአንድ ትውልድ ምልክቱ፤ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፤ ነፍስ ይማር፡፡
****
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ሰውዬው የሚጠየፉት ፓርቲ “አርፎ መኖር” የሚባለውን ነው፡፡ ሳያርፉ ኖረዋል፡፡ ሳይገዙ በክብር ተሸኝተዋል፡፡ እድሜን አሸንፎ የነብር ጣት ኾነው የኖሩት ኢትዮጵያዊ ሊቅ በሞት ተሸነፉ፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በሀገራቸው ጉዳይ መስፍነው የኖሩ ምሁር ናቸው፡፡ እንደ ተከበሩ ወደማይቀረው ዓለም የሄዱ፡፡

አንድ ሺህ ችግሮች ሊኖሩባቸው ይችላል፤ ሰውዬው ግን ክቡር ናቸው፡፡ የቱም የሚነሳባቸው ሀሳብ መፍትሔነታቸውን የማይጋርድባቸው፡፡ ሀገረሰባዊ እውቀትን ክብር በመስጠት ወደር የሌላቸው ሊቅ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን አንድ ሰው አይደሉም፡፡ የአንድ ትውልድ ምልክት ናቸው፡፡ በአንድ ዘውግ አይገለጹም፤ የብዙ እውቀት ማስመስከሪያ ኾነዋል፡፡ ይኽ ትውልድ ከዚያ የተቀባለቸው ሞገስም ነበሩ፡፡

ሰውዬው ከሦስት መንግስት ጋር ተጋፍጠዋል፡፡ በሦስትም መንግስት ሰውዬው ናቸው፡፡ አወዛጋቢ ንግግሮቻቸው ምናልባትም የሌላ ሰው ቢሆኑ ያ ሰው ዛሬ እንዲህ ላለው ክብር ባልበቃ፤ እሳቸው ግን ይሞግታሉ እንጂ አይሸሹም፡፡

የየዘመኑን ወጣት አታግለዋል፡፡ እያታገሉ አልጋ ይዘው ትግል ላይ ሳሉ ሲመስለን አልፈዋል፡፡ መርህ የእውቀት ሁሉ መሰረት መኾኗን በመኖር አስተምረዋል፡፡ ከዘራ ይዘው ሀገር በክብር እንድትቆም ቆመዋል፡፡

የፕሮፌሰር መስፍን ትልቁ ጸጋ ያገባኛል ባይነትን ለትውልድ ማስተማር ነው፡፡ ዝም አልልም ባይነትን አጋብተዋል፡፡ ትውልዱ ከፕሮፌሰር ሊማር የሚገባው ትልቅ እውቀት በሀገሬ ጉዳይ ባለቤት ነኝ ባይነትን ነው፡፡

የመንግስታቱ ከሰለሞን መመዘዝ አልያም የመሳሪያ ብዛት ወይም የሽብር ህግ ጋጋት ሲያልፍ ደግሞ ቤተ መንግስት ጋብዞ በማማለል አሁን ጸሐይ ወጣ ዓይነት አገልጋይነትን ድል አድርገው እንደፈለጉት በመኖር በማይፈልጉት ሞት ተማርከዋል፡፡ ፕሮፌሰር የሀገር አውራ ነበሩ፡፡ ሀገር ምልክቷን አጥታለች፡፡ ነፍሳቸውን ይማር፡፡

Continue Reading
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top