Connect with us

ሐበሻ ቢራ – የቡና ስፖርት ክለብን ለያዝነው ዓመት ስፖንሰር አደረገ

ሐበሻ ቢራ - የቡና ስፖርት ክለብን ለያዝነው ዓመት ስፖንሰር አደረገ

ስፖርት

ሐበሻ ቢራ – የቡና ስፖርት ክለብን ለያዝነው ዓመት ስፖንሰር አደረገ

የሐበሻ ቢራ አ/ማ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብን ለመደገፍ የሚያስችል የስፖንሰርሺኘ ስምምነት በጎልደን ቱሊኘ ሆቴል በዛሬው ዕለት ተፈራረመ።

ከሐምሌ 1/2012 እስከ ሰኔ 30/2013 ዓ.ም ለአንድ ዓመት በሚቆየው በዚሁ ስምምነት መሰረት ሐበሻ ቢራ አ/ማ ለቡና ስፖርት ክለብ በጠቅላላው 28 ሚልየን 250 ሺ ብር የስፖንሰርሺኘ ድጋፍ ያደርጋል።

ይህ ገንዘብ የስፖርት ክለቡ በዓመት ውስጥ የሚያከናውናቸውን ልዩ ልዩ ተግባራት ጨምሮ በተለያዩ ግጥሚያዎች ለተጨዋቾች የሚከፈሉ ሽልማቶችና የማበረታቻ ክፍያዎችን ያጠቃልላል።

ስምምነቱን በሐበሻ ቢራ አ/ማ በኩል አፌል አንበርብር የሽያጭ ስራ አስኪያጅ እና አቶ ገዛኸኝ ወልዴ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ስራ አስኪያጅ ተፈራርመዋል። በስነስርአቱ ላይ አቶ ክንፈሚካኤል ፀጋዬ የሐበሻ ቢራ የአዲስአበባ የሽያጭ ኃላፊ እና አቶ ሚኒልክ በሃብቱ የቡና ስፖርት ክለብ የቦርድ አባል ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

ሐበሻ ቢራ ከ8 ሺ በላይ ባለአክስዮን በማቀፍ ከአምስት አመት በፊት ወደስራ የገባ ሲሆን ፋብሪካው በቀጥታ ከ500 በላይ ሰራተኞች የስራ ዕድል ፈጥሯል።

የኢትዮጵያ ስፖርት ክለብ ከሌላው የሚለየው ገቢውን የሚያገኘው በራሱ መንገድ ነው ያሉት የክለቡ አመራሮች ከቡና ዘርፍ፣ ከስፖንሰርሺኘ፣ ከተለያዩ ሽያጮች፣ ከደጋፊዎችና ከሜዳ የሚገኙ ገቢዎች እንዳሉት ተገልጷል። በተጨማሪም ከ6 ሚልየን በላይ ደጋፊዎች እንዳሉትም በስነስርአቱ ላይ ተነግሯል።

የሐበሻ ቢራ አ/ማ የስፖንሰርሺኘ ድጋፍ ባለፉት ዓመታት ከአንድ ሚልየን ብር ገደማ ተነስቶ እያደገ በመምጣት ዘንድሮ ከ28 ሚልየን ብር በላይ መድረሱ በአዎንታነት ተጠቅሷል።

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top