Connect with us

የልደቱ አያሌው የፍ/ቤት ውሎ

ልደቱን ፖሊስ አለቅም ማለቱ ተሰማ
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

የልደቱ አያሌው የፍ/ቤት ውሎ

አቶ ልደቱ አያሌው አዳማ በሚገኘው የኦሮሚያ  ጠቅላይ ፍርድ ምስራቅ ችሎት በተጠየቀባቸው ይግባኝ ችሎት ቀርበዋል። በችሎቱ የአቶ ልደቱን ዋስትና ለማስከልከል አቃቢ ህግ ያቀረበውን ምክንያት ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ሰምቷል። አቃቢ ህግ አቶ ልደቱ ዋስትናው ቢፈቀድላቸው፣

1ኛ/  በዋስ ቢለቀቁ ምስክሮቼን ያስፈራራብኛል

2ኛ/ ዉጭ ህክምና ቀጠሮ ስላላቸው ሄደው ይቀሩብኛል

3ኛ/ የተያዘባቸው ህገ ወጥ ሽጉጥ ስለሆነ ዋስትና ያስከለክላል

4ኛ/ አቶ ልደቱ ቢወጡ በደጋፊዎቹ ምስክሮቼ ላይ ተፅዕኖ እንዲፈጠር ያደርጋሉ

በሚል ዋስትናው ውድቅ እንዲሆን የጠየቁበትን ምክንያት አስረድተዋል። በአቶ ልደቱ በኩል ጠበቆች  አቃቢ ህግ ያቀረበውን ጭብጥ በመቃወም ሰፊ መቃወሚያ አቅርበዋል። በመጨረሻ አቶ ልደቱ በአስተርጓሚ የአቃቢ ህግ ሃሳብ ተገልጦላቸው የሚናገሩት ነገር እንዳለ ፍርድ ቤቱ እድል ሰጥቷቸው አቶ ልደቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል። 

አቶ ልደቱ እስካሁን ከ10 ግዜ በላይ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን፣ በእስር ላይ ከ70 ቀን በላይ እንደሆናቸው ጠቅሰው አቃቢ ህግ ዋና አላማው እኔን በእስር ላይ በማቆየት ህይወቴ እንዲያልፍ ማድረግ ነው ብለዋል። ይህንንም ሲያብራሩ 

1ኛ/ ምስክሮቹ ቤቴ ላይ ፍተሻ ሲደረግ ታዛቢ የነበሩ ናቸው። መሳሪያው በእጄ መገኘቱን ባልካድኩበት ሁኔታ እንዴት ምስክር የተባሉትን ላስፈራራ እችላለሁ

2ኛ/ ውጭ ህክምና ቀጠሮ እንዳለኝ የተናገርኩት እኔ ነኝ። ከፍርድ ቤት ለመሸሽ ብፈልግ ይሄን ለምን እናገራለሁ። የተናገርኩት የፍርድ ቤት ቀጠሮ ሲሰጠኝ በቀጠሮዬ እንድገኝ የሚያስችል ሁኔታ እንዲኖር ነው።

3ኛ/ የተያዘባቸው ሽጉጥ ህገ ወጥ ነው ለተባለው አቃቢ ህግም መንግስትም እውነቱን ያውቁታለል። መንግስት ራሱ ሰጥቶ ነው ራሱ እየከሰሰኝ ያለው፣

4ኛ/ ደጋፊዎቹ ምስክሮች ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራሉ ብሎ ማለት ህገ ወጥነት ነው። ፓርቲያችን ህጋዊ ፓርቲ ሆኖ ለሃያ አመት የቆየ ፓርቲ ነው። እኔም ከ27 አመት በላይ ትግሉ ውስጥ የቆየው ግለሰብ ነኝ። ፓርቲዬ ለአንድም ቀን በህገ ወጥ ድርጊት ተከሶ አያውቅም። እኔም ላለፉት አመታት ከ5 ጊዜ በላይ ብታሰርም ሁሉንም በነፃ የወጣሁበት ነው። ስለዚህ በፓርቲዬም ሆነ በኔ ላይ የተሰነዘረው ወቀሳ ተቀባይነት የለውም። በባለፈው ስርአትም ውጭ ወጥቼ እንድቀር በተደጋጋሚ የተሞከረውን ሙከራ ያከሸፍኩት ለሰላማዊ ትግል አና ለህግ ተገዥ ስለሆንኩ ነው። በመሆኑም በእስር እንድቆይ የተፈለገው ወንጀል ስለሰራው ሳይሆን በፖለቲካ አስተሳሰቤ ነው። የሚፈለገው እኔን በወንጀል ከሶ ማስቀጣት ሳይሆን የፍርድ ቤት ሂደቱን እያራዘሙ፣ ይግባኝ እየጠየቁ እስር ቤት በማቆየት ህይወቴ እንዲያልፍ ማድረግ ነው ብለዋል። ፍርድ ቤቱም የቀረበውን መከራከሪያ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ለመስከረም 26 ከጠዋቱ 3 ሰአት ቀጠሮ ሰጥቷል። ነገ የምስራቅ ሸዋ ፍርድ ቤት ቀጠሮ አለ ምን እንደሚባል እንሰማለን። የነገ ሰው ይበለን።(ምንጭ :-አዳነ ታደሰ የኢዴፓ ሊቀመንበር ፌቡ ገፅ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top