Connect with us

የኢትዮጵያዊነቷን ምልክት-ወንጂን አለሁ እንበላት፤

የኢትዮጵያዊነቷን ምልክት-ወንጂን አለሁ እንበላት፤

ማህበራዊ

የኢትዮጵያዊነቷን ምልክት-ወንጂን አለሁ እንበላት፤

የኢትዮጵያዊነቷን ምልክት-ወንጂን አለሁ እንበላት፤
****
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰለጠነች መንደር ያየሁት ወንጂን ነበር፡፡ ያኔም ግን ወንጂ መልኳ ዥንጉርጉር ነው፡፡ ከደሳሳ የኩሪፍቱ መንደሮች ጀርባ ቅንጡ የሽቦ ግቢ ቪላዎች አሉ፡፡ አንዱ በሌላው አይቀናም፡፡ ዛሬ ብዙ ሆኖ አንድ ከተማ ገብቶ አንድ ትልቅ ሆቴል ማንደድ ለከተሞቻችን ብርቅ አይደለም፡፡ ወንጂ ግን አጥርን በሽቦ ከልሎ ቅንጡ ኑሮ መኖር ብርቅ አይደለም፡፡

አዋሽን የተሻገረ ሰው አንድ የጋራ ነገር ይመለከታል፡፡ ጥርሱ ቼኮላት የመሰለ ፈገግታና አብሮ መኖር የገነነበት እሴት፤ እዚህ ላብ እንጂ ዘመድ ዋጋ የለውም፡፡ እዚህ ጥሪትን አብሮ መብላት በየሰው ልብ በክብር ያለ ጸጋ ነው፡፡

“ብታጣ ብታጣ አገዳ በልተህ ታድራለህ፤” ይሉ ነበር ያኔ የወንጂ ጎረምሶች፡፡ ከሸዋ እስከ ገፈረሳ ራስን በሰፈር ጓድ እንጂ በብሔር ማዋቀር ለዚህች የላብአደሮቹ ከተማ ነውር ድርጊት ነው፡፡ የካምፕህ ልጅ ወንድምህ ነው፡፡ አንደኛ መንገድ ኖረህ መስታወት ሰፈር ስትገባ በአንድ ጊዜ የሁለት ህብረት አባል መሆን እንጂ ሃድያ መንደር ከንባታ ሰፈር ብሎ ነገር የለም፡፡ አማራና ትግሬነትህ የፋብሪካውን ደውል ያህል ዋጋ የለውም፡፡

ወንጂን እንዲህ ባለ ባህሏ ተጠየፏት፡፡ ብዙ መከራዎችን አለፈች፡፡ በቀል በቆቃ በር እያለፈ ህይወቷን አመሳቀለው፡፡ ፋብሪካዋ ደካማ ተባለ፡፡ ደማቋን ምድር ባድመ አደረጓት፡፡ ወንጂን ጠፍ የማድረግ ስልቱ የተቀናጀ ነው፡፡

ከሸዋ እስከ ገድገዲ ወንጂ ልጆች እልፍ ሆነዋል፡፡ ከጎርጎ ጫፍ እስከ ኩሪፍቱ ብዙ ናቸው፡፡ እንደ አደገኛ ጎረፍ ሃያላን፡፡ ብዙ ምሁራንን ያፈራችው ወንጂ ዛሬም ከጉስቁልና ታደጉኝ ትላለች፡፡ እምነትና ብሔር የልዩነት ምክንያት ያልሆኑባት ቀደምቷ የስራ መዲና በፍልስፍናዋ ሳቢያ በብዙ ነገር መከራን ተጋፍጣለች፡፡ ልማት ለወንጂ ናፍቆት ሆኗል፡፡ እድገትና ብልጽግና በብልጽግና ሰዎች እንኳን ያልታቀደላት ከተማ ናት፡፡ ወንጂን ከተማ ስላት ይቀልብኛል፡፡ ሀገር ናት፤

የወንጂ ልጆች አሁን ከየአሉበት ተጠራርተዋል፡፡ እንደ ወንጂ ያሉ የአንድነታችንን ማኅተሞች ከፍ አድርገን ብንሰቅላቸው ክብሩ ብቻ ሳይሆን ጥቅሙም የኢትዮጵያ ነው፡፡ ወንጂ የኢትዮጵያዊነት ምልክት ናት፡፡

እዚያ ከተከዜ መለስ እስከ ባሮ ባለው ምድር ያለ የሀገር ልጅ ወዝ አብሮ ተቃብቷል፡፡ እዚያ ከአይማ እስከ አቢ ሐይቅ ምድሩን የኖረበት የሀገር ሰው ሀገሬ ብሎ ኖሮበታል፡፡ እዚያ ነውር ሳይሆን ላብ፣ ጥላቻ ሳይሆን ፍቅር ነግሶበታል፡፡ ወንጂን አለሁ እንበላት፤ የሁላችን ምልክት ናትና፤

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top