Connect with us

ጠ/ሚር ዐቢይ ኢትዮጵያውያን የሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተባባሪዎች እንዳይሆኑ አሳሰቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያውያን የሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተባባሪዎች እንዳይሆኑ አሳሰቡ
Photo: Ethiopian Reporter

ኢኮኖሚ

ጠ/ሚር ዐቢይ ኢትዮጵያውያን የሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተባባሪዎች እንዳይሆኑ አሳሰቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተባባሪዎች እንዳይሆኑ አሳስበዋል።

የጥሬ ገንዘብ ለውጥ በሚካሄድበት በዚህ ወቅት ሁሉም ሀገር ወዳድ ዳያስፖራዎች የውጪ ምንዛሬን በሕጋዊ መንገድ ብቻ እንዲልኩ ነው ጥሪ ያቀረቡት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህም ዜጎች የሕገ ወጥ ገንዘብ ልውውጥ አስተላላፊ ከመሆን እንዲቆጠቡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ መስከረም 04 ቀን ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 የብር ኖቶች የሚተኩ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶችና አዲሱን የ200 ብር ኖት ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ እንዳሉት አዲሶቹን የገንዘብ ኖቶች ይፋ ማድረግ ያስፈለገው ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ሙስናንና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቆጣጠር ያግዛሉ ማለታቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም አዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች እንዲኖራቸው የተደረጉት የደኅንነት ገጽታዎች አመሳስሎ ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት እንደሚያግዙ መጠቆማቸውን የኢዜአ ዘገባ የመለክታል።

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top