Connect with us

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነባሮቹን የብር ኖቶች በአዲስ የመቀየር ሥራ በይፋ ጀመረ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ነባሮቹን የብር ኖቶች በአዲስ የመቀየር ሥራ በይፋ ጀመረ
Photo: Social media

ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነባሮቹን የብር ኖቶች በአዲስ የመቀየር ሥራ በይፋ ጀመረ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ነባሮቹን የብር ኖቶች በአዲስ የመቀየር ሥራ በይፋ ጀመረ

~ከአምስት ሺህ ብር በላይ መቀየር የሚፈልግ የባንክ አካውንት ሊኖረው ይገባል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ አቤ ሳኖ በትላንትና ዕለት አዲስ አበባ ቅርንጫፍ በመገኘት አዲሱን የብር ኖቶች ሥርጭት አስጀምረዋል፡፡

አዳዲስ የብር ኖቶችን በመጠቀምም የመጀመሪያዎቹ ሆነዋል፡፡

በትላንትናው እለት የተጀመረው አዳዲስ የብር ኖቶችን የማሰራጨት ሥራ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ክልሎች ማሰራጨት እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ገልፀዋል፡፡

ይህ ከፍተኛ ዝግጅት የሚጠይቅ የብር ኖቶችን የመቀየር ሥራ በተሟላ መልኩ ተጠናቅቆ ስርጭት በመጀመሩም ደስታ እንደተሰማቸው ዶ/ር ይናገር አክለው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ አቤ ሳኖ በበኩላቸው ህብረተሰቡ አሮጌውን ብር በመመለስና አዳዲሶችን የብር ኖቶች በመውሰድ ብሩን የመቀየር ሂደት እንዲያቀላጥፍ አሳስበው፤ ከአምስት ሽህ ብር በላይ መቀየር የሚፈልግ ተጠቃሚ ነባር የባንክ ደብተር ከሌለው አዲስ መክፈት እንደሚጠበቅበትም ገልፀዋል፡፡(ኢት ንግድ ባንክ)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top