Connect with us

በኦሮሚያ ቆመው ዝምታን በመምረጥ ንጹሃንን ያስጨረሱ

በኦሮሚያ ግርግሩን ተከትሎ የታመሱት ከተሞች

ፓለቲካ

በኦሮሚያ ቆመው ዝምታን በመምረጥ ንጹሃንን ያስጨረሱ

ባሳለፍነው አመት ያስተናገድነውን እልቂት ቆመው ዝምታን በመምረጥ ንጹሃንን ያስጨረሱ እንዳሉ ሁሉ ለሰላም ዋጋ ከፍለው ብዙ ከተሞችን ከአመጽ ያዳኑም የኦሮሚያ የጸጥታ ሃይሎች አሉ፡፡
ከስናፍቅሽ አዲስ

የኦሮሚያ ክልል ለክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጸጥታ አካላት የሰጠውን እውቅና ተከትሎ እንቆቅልሽ የሆነባቸው የዚህ መንደር ዜጎች ቅሬታቸውን አንጸባርቀዋል፡፡ እርግጥ ነው ሰላም አስከባሪ ባለበትና የህግ የበላይነት ተከብሯል ተብሎ በሚታመንበት ሀገር እንዲህ ያለው ዘግናኝ አጋጣሚ አይፈጠርም፡፡

ከዚህ በመነሳት የጸጥታ መዋቅሩ ምን ሰርቷል ብለው የሚሞግቱም አሉ፤ ይሁን እንጂ አጸያፊ የጸጥታ ሃይሎች እንዳሉት ሁሉ ተንበርክከን የምናመሰግናቸው ወገኖችም አሉን፡፡

በኦሮሚያ የነበረው ችግር ጎልቶ ከጸጥታ ጓዶች ጋር ሊነሳ የሚችለው የሻሸመኔው ነው፤ በሻሸመኔ በርካታ የጸጥታ ሃይሎች ቆመው እየተመለከቱ የንጹሃን ደም ሲፈስ ምንም ዓይነት እርምጃ አለመውሰዳቸው ደጋግሞ ሲነገር ሰምተናል፡፡

ብዙ ቦታዎች ደመወዝ ያነሰውና እንደ አሸን በጎሳ ፖለቲካ እየተጠመቀ የሚወጣ የክልል ፖሊስ ሙያዊ ስነ ምግባሩ ላይ ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲነሳም ቆይቷል፡፡

በኦሮሚያ ግርግሩን ተከትሎ የታመሱት ከተሞች ጥቂት ናቸው፡፡ ብዙ አካባቢዎች የኦሮሚያ የጸጥታ ሃይሎች ከፍተኛ ስራ ሰርተው ሀሳቡ ምኞት ብቻ ሆኖ ቀርቷል፡፡

ውጪ ሀገር ተቀምጠው መንገድ ዝጋ እያሉ ለአመጽ የሚያነሳሱትን ምኞት ቅዠት ብቻ አድርገው በማስቀረትም የኦሮሚያ የጸጥታ ጓዶች ይመሰገናሉ፡፡

በዚያ አውሬዎች የሰው ደም ለመጠጣት ሲንቀዠቀዡ አብሮ የጠጣው የጸጥታ አካል ብቻ ሳይሆን ይህንን እኩይ አላማም ያከሸፈ የኦሮሚያ ጸጥታ መዋቅር ምስጋና ይገባዋል፡፡

በየከተማው የታሰበው አመጽ ጥቂት ቦታዎች ላይ ብቻ ሆኖ የቀረው ብዙ ከተሞች በሚገኙ የክልሉ የጸጥታ ሃይልና ህዝብ ቁርጠኛነት ነው፡፡

የኦሮሚያ ክልል ዛሬም ድረስ ዜጎች በሰላም እንዳይኖሩ እንቅፋት የሆኑ አረመኔዎች ፋታ ቢነሱትም ይህንን በመታገልና በጽናት ሀሳቡን በማክሸፍ አስተዋጽ እያበረከቱ ህይወት እየገበሩ ያሉ የክልሉ የጸጥታ ሃይሎች ብዙ ናቸው፡፡ ለእነሱ ክብር ይገባል ምክንያቱም ከሜዳሊያ በላይ ናቸውና፤

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top