Connect with us

መንግሥት ተጎጂዎች የሚሹተትን ፍትሕ በማስፈን ቁርጠኝነቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳሳደረበት ሀገረ ስብከቱ ገለጠ

መንግሥት ተጎጂዎች የሚሹተትን ፍትሕ በማስፈን ቁርጠኝነቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳሳደረበት ሀገረ ስብከቱ ገለጠ
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

መንግሥት ተጎጂዎች የሚሹተትን ፍትሕ በማስፈን ቁርጠኝነቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳሳደረበት ሀገረ ስብከቱ ገለጠ

የመንግሥት ባለሥልጣናትና መንግሥት የሚቈጣጠራቸው ብዙኃን መገናኛዎች የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ማውገዝ ሲገባቸው ተራ ዝርፊያና የሁለት ወገኖች ግጭት አስመስለው በማድበስበስ ማቅረባቸው በጉዳቱ ሰለባዎች ላይ ተጨማሪ የሞራል ስብራት ከማስከተሉም በተጨማሪ መንግሥት አጥፊዎችን ለፍርድ በማቅረብ ተጎጂዎች የሚናፍቁትን ፍትሕ የማስፈን ቁርጠኝነቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳሳደረበት የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ገለጠ።

ፍትሕ ርትዕ ያስተማረችና አገራችን በታላቅ ክብርና ሞገስ እንድትታወቅ ያደረገች ቤተክርስቲያን ፍትሕ መነፈጓን ያስታወቀው የሀገረ ስብከቱ መግለጫ አብያተክርስቲያን በጠራራ ፀሐይ እንደጧፍ እንደሚነዱና ካህናትና ምእመናን በአደባባይ እንደሚታረዱ ገልጧል።

“ፌደራል መንግሥትና የሚመለከታቸው አካላት ባሳዩት ቸልተኝነት የበርካታ ዜጎች የማይተካ ሕይወት ማለፉንና በብዙ ድካም ያፈሩት ንብረት በአንድ ቀን ጀምበር እንዲወድም ምክንያት መሆኑን ያስገነዘበው የሀገረ ስብከቱ መግለጫ ቤተክርስቲያን የገጠማትን ችግር ለመፍታት በመሪ ዕቅድ መመራትና በጥናት ላይ የተደገፈ መዋቅራዊ የአስተዳደር ለውጥ ማካሔድ ይኖርባታል” ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ለተጎጂዎች የሚያደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰበው የሀገረ ስብከቱ መግለጫ የደኅንነት ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች እየለየ የሚደርሰውን ጉዳት ለመንግሥትም ሆነ ለሚመለከታቸው ሁሉ የሚያሳውቅና ለክርስቲያኖች መረጃ የሚያቀብል ጠንካራ ተቋም መቋቋም እንደሚኖርበትም አሳስቧል።

መንግሥት ተጎጂዎችን መልሶ እንዲያቋቁም ያሳሰበው የሀገረ ስብከቱ መግለጫ ወንጀለኞችን በአፋጣኝ ለሕግ እንዲያቀርብ፣ ክርስቲያኖችን ለአደጋ የሚያጋልጡ የጥላቻ ንግግሮችንና ቅስቀሳዎችን በሚያደርጉ አካላት ላይ የማያዳግም ርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል። በአገራችን የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ዜጎች እምነታቸውን በአደባባይ የመግለጥ መብታቸውን የሚጻረሩ ጽንፈኞችን ድርጊት እንዲቃወሙ ጥሪ አድርጓል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top