Connect with us

በአዲስአበባ ርችት መተኮስ ተከለከለ

በአዲስአበባ ርችት መተኮስ ተከለከለ
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

በአዲስአበባ ርችት መተኮስ ተከለከለ

በአዲስአበባ ርችት መተኮስ ተከለከለ

ለፀጥታ ሲባል በአዲስ አበባ ማንኛውም ግለሰብ ርችት መተኮስ እንደማይችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት የሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት መግለጫ÷ ርችትን ምክንያት በማድረግ የሽብር ጥቃት ለማድረስ እየተዘጋጁ ያሉ ግለሰቦች መኖራቸውን ፖሊስ በጥናት ደርሶበታል ብለዋል።

ስለሆነም ወንጀልን ለመከላከል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ማንኛውም ግለሰብ ርችት መተኮስ አይችልም ብለዋል። ይህንን ተላልፎ ሪችት የሚተኩስ ማንኛውም ሰው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚውል ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜናም በአዲስ አበባ በአስሩም ክፍለ ከተማ በጥናት በተደረገ ፍተሻ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።

በፍተሻው አንድ ቦምብ እና አራት ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የተናገሩት።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም የተጠረጠሩ 180 ግለሰቦች ተይዘው ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም አመላክተዋል።

ዋና ኢንስፔክትር ማርቆስ አያይዘውም ህብረተሰቡ የራሱን ሰላም በመጠበቅ፣ ሰላምን ሊያውኩ የሚችሉ ወንጀለኞችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት እንዲተባበርም ጥሪ አቅርበዋል።

#FBC

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top