Connect with us

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቹን መከረ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቹን መከረ
Photo: Social Media

ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቹን መከረ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከ2011 ዓ.ም ታህሳስ ወር ጀምሮ በአራት ተከታታይ ዓመታት ተከፋፍሎ ተግባራዊ የሚደረግ አዲስ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ይህ ማስተካከያ የተተገበረው የደንበኞች የመክፈል ዓቅማቸውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ነው፡፡

የመኖሪያ ቤት ደንበኞች በየወሩ የሚከፍሉት የፍጆታ ሂሳብ የተጠቀሙበትን የኤሌክትሪክ ሃይል እና የአገልግሎት (በተለምዶ የቆጣሪ) ክፍያ ድምር ነው፡፡

ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ሃይል ፍጆታ ሂሳብ ለቅድመና ለድህረ ክፍያ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች ተመሳሳይ ዋጋ ቢኖረውም የአገልግሎት ክፍያው ግን ደንበኞች በሚጠቀሙበት የቆጣሪ አይነት እና በሰዓት በሚጠቀሙት ኪሎ ዋት መጠን መሰረት ይለያያል፡፡

በዚህ አግባብ በመኖሪያ ቤት የታሪፍ መደብ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች በሰዓት ከ50 ኪሎ ዋት በታች ከተጠቀሙ ለአገልግሎት በወር 10 ብር የሚከፍሉ ሲሆን፤ በሰዓት ከ50 ኪሎ ዋት በላይ የሚጠቀሙት ደግሞ 42 ብር ይከፍላሉ፡፡

የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች በሰዓት ከ50 ኪሎ ዋት በታች ከተጠቀሙ የአገልግሎት ክፍያቸው 3.50 ብር ሲሆን፤ በሰዓት ከ50 ኪሎ ዋት በላይ ሲጠቀሙ 14.70 ብር ይከፍላሉ፡፡ ይህም የአገልግሎት ክፍያ ካርድ ሲሞሉ ቀድመው ከሚገዙት (አድቫንስ) የኃይል መጠን ላይ በወር አንዴ ተቀናሽ የሚደረግ ይሆናል፡፡

የተቋሙ የኢነርጂ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ አባይ አድማሱ የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች የሚገዙት የኤሌክትሪክ ኃይል በቅድሚያ (አድቫንስ) የሚከፈል መሆኑ ለተቋሙ የገንዘብ አሰባሰብ ስርዓት አዎንታዊ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አያይዘው እንደተናገሩት አንዳንድ የቅድመ ክፍያ ደንበኞች ኃይል ለመግዛት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ላለመመላለስ ብለው አንድ ጊዜ በከፍተኛ የብር መጠን ኢነርጂ እንደሚገዙ ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ደንበኞች ወደ ማዕከሉ በማይመጡባቸው ወራት ሳይከፈል የሚጠራቀመው የአገልግሎት ክፍያ ተደምሮ እንዲከፍሉ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ይህም ደንበኞች ከሚገዙት የገንዘብ መጠን ስለሚቆረጥ ኃይል በሚገዙበት ጊዜ ካርዳቸው ላይ የሚሞላው ገንዘብ ዝቅ ሊል እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ለምሳሌ አንድ ደንበኛ ለ6 ወራት ካርድ ባይሞላ እና በሰዓት ከ50 (ሀምሳ) ኪሎዋት በላይ ቢጠቀም (የአገልግሎቱ 14.70 ብር) ሲሰላ ከሚገዛው የኃይል መጠን ላይ (6×14.70=88.20) ሰማንያ ስምንት ብር ከሀያ ሳንቲም ይቀነስበታል ማለት ነው፡፡

በመሆኑም የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ከመሰል ተጨማሪ ወጪ እንዲድኑ ሁልጊዜ በየወሩ ኃይል ገዘተው እንዲጠቀሙ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

(የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top