Connect with us

የኢትዮ ቴሌኮም 5 በመቶ ድርሻ በኢትዮጵያውያን በአክስዮን እንዲያዝ ተወሰነ

የኢትዮ ቴሌኮም 5 በመቶ ድርሻ በኢትዮጵያውያን በአክስዮን እንዲያዝ ተወሰነ
Photo: Ethiopian Reuters

ኢኮኖሚ

የኢትዮ ቴሌኮም 5 በመቶ ድርሻ በኢትዮጵያውያን በአክስዮን እንዲያዝ ተወሰነ

የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ማሻሻያ ስራዎች ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ውይይት ተካሂዷል።

ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ለማዘዋወር እና ተጨማሪ የቴሌኮም ኮርፖሬሽኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የተወሰነው ውሳኔ ሂደት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ተገምግሟል።

በውይይቱ ላይ ኢትዮ ቴሌኮም በከፊል ወደ ግል ሲዘዋወር 40 በመቶ ደርሻ ለአለም አቀፍ ኩባንያዎች እንደሚተላለፍ ተነግሯል።

5 በመቶ ድርሻ ደግሞ ለኢትዮጵያዊያን ዜጎች በአክስዮን ይሸጣል ነው የተባለው።
ይህ 5 በመቶ አክስዮን በጥቂት ግለሰቦች የሚያዝ ሳይሆን ሁሉም ዜጋ እንደ አቅሙ የሚሳተፍበት መሆኑ ተጠቁሟል።

ቀሪውን 55 በመቶ ድርሻ መንግስት እንደያዘው እንደሚቀጥልም ተነግሯል።

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርን ለማዘመን የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ከማስተላለፍ ባሻገር ለሁለት አዳዲስ ኦፕሬተሮች ፈቃድ እንደሚሸጥ ተገልጿል።

ሁለቱ አዳዲስ ኦፕሬተሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምና ልምድ ያላቸው እንዲሁም ቴክኖሎጂዎችን የሚያሸጋግሩ ይሆናሉ ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፈቃድ የመስጠትም ሆነ በከፊል የማዘዋወር ስራዎች ከሌብነት በፀዳ፣ ሙያዊ አካሄድን በተከተለ እና የምናስበውን ጥቅም ለሀገር ማስገኘት በሚችል መልኩ ይከናወናል ብለዋል።

ዘርፉን ሊብራላይዝድ የማድረግ ሂደቱ የፓሊሲ ግፊት የሌለበት እና በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የቀረቡ መርሆች እና አቅጣጨዎች ላይ ተመስርቶ የሚሄድ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።(FBC)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top