Connect with us

በቢሾፍቱ ከተማ ኩሪፍቱ ሆቴል ሲካሄድ የቆየው የአምባሳደሮች ስብሰባ ተጠናቀቀ

በቢሾፍቱ ከተማ ኩሪፍቱ ሆቴል ሲካሄድ የቆየው የአምባሳደሮች ስብሰባ ተጠናቀቀ
Photo: Social Media

ዜና

በቢሾፍቱ ከተማ ኩሪፍቱ ሆቴል ሲካሄድ የቆየው የአምባሳደሮች ስብሰባ ተጠናቀቀ

በቢሾፍቱ ከተማ ኩሪፍቱ ሆቴል ሲካሄድ የቆየው የአምባሳደሮች ስብሰባ ተጠናቀቀ

”ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኳችን ለአገራዊ ብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል ከነሀሴ 18 ቀን 2012 ዓም ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ ኩሪፍቱ ሆቴል ሲካሄድ የቆየው የውጭ ጉዳይ የዋናው መ/ቤት የስራ ሃላፊዎች እና የሚሲዮን መሪዎች ዓመታዊ ስብሰባ ዛሬ ሰኞ ጳጉሜ 2 ቀን 2012 ዓም ተጠናቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተገኝተው የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል።

ክቡር አቶ ገዱ በንግግራቸው በመገባደድ ላይ ያለው የ2012 ዓ.ም. ዓለም ብዙ ውጣ ውረዶች ያለፈችበትና የተለምዶው የዲፕሎማሲ ስራ ከፍተኛ ተግዳሮት የገጠመበት ዓመት እንደነበር ገልጸዋል።

የበጀት ዓመቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዕቅድ አፈጻጸማችን እና የዲፕሎማሲ እንቅስቃሲያችን አስቀድመው ባልተገመቱ ተግዳሮቶች የታጀበ ቢሆንም በጥቅሉ ሲታይ ውጤታማ እንደነበርም ክቡር አቶ ገዱ ጠቅሰዋል።


ኮቪድ 19ን ለመከላከል እና ተየታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዓመት ሙሊት በስኬት አንዲጠናቀቅ የፋይናንስ እና የማቴሪያል ድጋፎችን ከማስገኘት የኢትዮጵያን አቋም ከማስረዳት እንዲሁም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን በያሉበት ሀገር በቫይረሱ እንዳይጠቁ ችገር የገጠማቸውንም ለማገዝ የተደረጉ እንቅስቃሴዎች ፋይዳቸው ከፍ ያለ እንደነበር ክቡር አቶ ገዱ አንስተዋል።


ኢትዮጵያ ብዙ ፈተናዎች እና ችግሮች ሲደራረቡባት እንቅፋቶችን ሁሉ አሸንፋ እና ከተግዳሮቶቿ እና ፈተናዎቿ ልቃ የምትገኝ ሀገር መሆኗንም በንግግራቸው አንስተዋል አቶ ገዱ። ሀገርን በኣለም አደባባይ ወይም በሌላ ሀገር ወክሎ መገኘት ታላቅ ዕድልና ክብር በመሆኑ ተልዕኳችንን ለመወጣት በሚጠበቅቅብን ልክ መንቀሳቀስ እንደሚገባም ገልጸዋል።


በነበረው ቆይታ በተሰጠው የመደመር ስልጠና መሰረት መ/ቤቱ የተሰጠውን ተልዕኮ ዕውን ለማደረግ የ2013 ውጤት ተኮር ዕቅድ እስከ ፈጻሚ ግለሰብ ድረስ በተቻለ ፍጥነት ካስኬድ በማድረግ በበጀት ዓመቱ ከ2012 የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አቶ ገዱ በንግግራቸው አሳሰበዋል።


የቢሾፍቱ ቆይታችን የተሳካ እንዲሆን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አመራር፣ የቢሾፍቱና አካባቢዋ ነዋሪዎች እንዲሁም የኩሪፍቱና የአዱላላ ሪዞርቶች አመራርና አባላትን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አቶ ገዱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በ2013 አዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ የምንገኝ መሆኑን በማስታወሰ አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የደስታ፣ የብልጽግና፣ ሀገራችን ያሰበችውን ሁሉ የምታሳከበት እንዲሁም በዋናው መ/ቤት እና በመላው ዓለም የሚገኙ ሰራተኞችም ስኬታማ ዘመን እንዲሆንላቸው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ምንጭ:-  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top