Connect with us

ከሕወሓት የተወረሰ ድራማ ቀጣይ ክፍል

ከሕወሓት የተወረሰ ድራማ ቀጣይ ክፍል
Photo: Social Media

ባህልና ታሪክ

ከሕወሓት የተወረሰ ድራማ ቀጣይ ክፍል

#የይቅርታ_ቀን_በሸራተን_አዲስ
( ከሕወሓት የተወረሰ ድራማ ቀጣይ ክፍል )

ጋዜጠኛውና ጸሐፌ ተውኔቱ ቴዎድሮስ ተክለ አረጋይ

እንዲህ ያሉ ድራማዎች መቼ ከዚህ ሀገር እንደሚወገዱ አላውቅም። ከሕወሓት ሁሉን ነገር ስናጥላላ ምነው ይህን ድራማቸውን ኮረጅን ? ” የከፍታ ዘመን ” ያልንበት ዓመት ውድቀት ነበር በሀገራችን ። አምና ” የሰላም ቀን ” አክብረን ነበር። የእልቂት አበላ ነበር በሀገራችን የወረደው።

ዘንድሮ ደግሞ ” የይቅርታ ቀን ” እያልን ድራማውን ቀጠልን ። ለማን ነው ይቅርታ የምናደርገው ? ወንጀለኞችን ? ሌቦችን ? በዳዮችን ? ማንን ? መንግሥት ከዚህ ድራማ ወጥቶ ሕግ ማስከበር ነው ያለበት ። ይቅርታ መጥፎ ስለሆነ አይደለም ።

መንግሥት ግን ከይቅርታ በላይ ቀዳሚ ተግባሩ ሕግ ማስከበር መሆን አለበት ። ይቅርታ በአግባቡ ካልተያዘ ወንጀል መሸሸጊያም ይሆናል ። የሀይማኖትና የሲቪል ተቋማት ደግሞ ቀን ከሌት ይቅርታን መስበክ ይጠበቅባቸዋል ።

መንግሥት ከይቅርታም በላይ ሕግ ማስከበር አለበት ። ቀዳሚ ስራው እሱ ነው። መድረክ መሪው ረ/ፕሮፌሰር ” ይቅርታ ማድረግ ዝቅ ማለትን ፣ ከልብ መሰበርን ይጠይቃል ” ብለዋል ። በቅድሚያ እሳቸው ራሳቸው የተናገሩትን ይተገብሩታል ? ድራማ የሚሆንብኝ ለዚህ ነው ።

እንደእኔ ለኢትዮጵያ መንግሥት ከይቅርታ ይልቅ ” ሕግን የማስከበር ቀን ” ነው የሚያስፈልገው። ድራማም ቢሆን እሱው ይሻላል።

 

የአ/አ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ የይቅርታ ቃል!

ለመላው የከተማችን ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች በከተማዋ አስተዳደር አማካኝነት ለተፈጠሩ ስህተቶችና የአስተዳደር ግድፈቶች የምህረት ወር ተብላ በምትታወቀው በወርሃ ጳጉሜ የመጀመሪያዋ ቀን ላይ ከፊታችሁ ቆሜ ይቅርታ እንድታደርጉልኝ በታላቅ አክብሮት እጠይቃለሁ። #ይቅርታ_እላለሁ_ይቅር_እላለሁ!


“ይቅርታ ይሁንልን!” ታከለ ኡማ (የቀድሞ የአ/አ ም/ከንቲባ)

“ውድ የከተማችን ነዋሪ ወገኖቼ፦

የኢትዮጵያውያን ሁሉ መዲና የሆነችውን ታላቅ ከተማ የማስተዳደርን ዕድል ላለፉት ሁለት ዓመታት በማግኘት ለማገልገል በመቻሌ ትልቅ ክብር ይሰማኛል።

ወደዚህ ኃላፊነት አከራካሪ በሆነ መንገድ ብመጣም፤ በወሬ ሳይሆን በሥራ፣ በብሔር ሳይሆን በኢትዮጲያዊነት የሚያምነው መልካምና ሰው ወዳድ ሕዝብ ጋር በፍቅር አብሮኝ ስለሠራና ስላሠራኝ ምስጋናዬ ሁልጊዜም ከፍ ያለ ነው።

አሁን በሥራ ላይ ያለው በእህቴ በወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሚመራው አስተዳደር የዛሬውን ቀን (ጷግሜ 1, 2012) “የይቅርታ ቀን ” ብሎ በሰየመው መሠረት፣ እኔም እንደከተማው ነዋሪና የቀድሞ አገልጋያችሁ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ ይቅርታ ይሁንልን እላለሁ።

ከተማዋን በማስተዳደር ኃላፊነቴ ወቅት እንዲሁም እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ባለማወቅ ለበደልኩት ለማንኛውም በደል ይቅርታን በትህትና እጠይቃለሁ።

እኔንም ለበደሉኝ፤ ያለበደሌ ለከሰሱኝ፣ ያለ ተግባሬ መጥፎን ስም ሰጥተው ላሳጡኝ፤ ሕዝብን ለማገልገል በምተጋበት ወቅት አላስፈላጊ ጦርነትን በመክፈት ሲያደክሙኝና አላሠራ ሲሉኝ ለነበሩት ሁሉ ከልብ የሆነ ይቅርታን አድርጊያለሁ።

የአዲሱ አመት የምህረት፣ የፍቅርና የአንድነት አመት ይሁንልን። ከስህተታችን የምንታረምበት፣ ካለፈው ተምረን ወደፊታችንን የምናሳምርበት ይሁንልን።”

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top