Connect with us

ዛሬ የአመቱ የመጨረሻ ቅዳሜ

ዛሬ የአመቱ የመጨረሻ ቅዳሜ
Photo: DW/A

ማህበራዊ

ዛሬ የአመቱ የመጨረሻ ቅዳሜ

ዛሬ የአመቱ የመጨረሻ ቅዳሜ-
ዘፋኙ እንዳለው ቅዳሜ ትደገም፤ 2012ን ግን ለዘለዓለም አያሳየን፡፡
***
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ዛሬ የከባዱ አመት የመጨረሻ ቅዳሜ ነው፡፡ ያለፉት ብዙ ቅዳሜዎች በዚህ አመት ብዙ መዓት የሰማንባቸው የስቅለት ዕለት ነበሩ፡፡ የመጨረሻውን ቅዳሜ በስስት ሳይሆን በደስታ እንሸኘዋለን፡፡ እርግጥ ዘፋኙ እንዳለው ቅዳሜ ትደገም ያ 2012 ግን መቼም አይደገም መቼም አንየው መቼም አያገናኘን፡፡

2012 ዝም ብሎ ያለፈ አመት አይደለም፡፡ ብዙ ያጣንበት ብዙ የሆንበት ብዙ የተጎዳንበት አመት ነው፡፡ ባቢሎን ሆነን መደማመጥ አቅቶን ጥላቻ በምድራችን ነግሶ እኛ የተዋረድንበት አመት ነው፡፡

ይህንን አመት መቼም በሀገራችን ምድር ዳግም አይመልስብን፡፡ አሁን እንኳን አመቱን ልንሸኘው ጫፍ ደርሰን እጅግ ከባድ መከራ እያስተናገድን ነው፤ ከዳሰነች እስከ አፋር ከኦሞ እስከ አዋሽ ጎርፍ ስንቱ ቤት እንደ እንግዳ ገብቶ እንደ ጠላት ህይወት አተራምሷል፡፡

ወገኖቻችንን አስቧቸው አመቱ ሊያልፍ ነው ብለው የሰቀቁንን ዘመን ሲሸኙ በወሩ መጨረሻ በጳግሜ በራፍ ከታችኛው አዋሽ የጀመረው መአት መካከለኛው አዋሽን አዳርሶ ላይኛው አዋሽ ገባ ከወንጂ መንደሮች እስከ መተሀራ አዲስ ከተማ ከመርቲ ውብ ሰፈሮች እስከ ደበል ብቻ አዋሽ ሰውን ከቀዬው አስወጣ፡፡

እኛ ለእኛ ተጨካከንን ከእኛ በተረፈው ተፈጥሮ ጨከነ፡፡ ብዙ መአት ገጠመን፡፡ አፋችን ተለጎመ፤ ህብረታችን ተመታ፡፡ ንጹሃን ሞቱ፤ ተስፋ ያለው ተቀጨ፡፡ ሞት ቀለለ፡፡ የምንወደውን በማንወደው መልኩ ብቻ ሳይሆን ሁላችን በምናፍርበት አግባብ አጣን፡፡ 2012

ከዚህ አመት አንድ ያተረፍነው ነገር የለም፡፡ ካተረፍንም ሞት ገብረን ህይወት ሰጠን ክቡር ደም አፍስሰን ነው፡፡ በዚህ ሰቀቀን ውስጥ የታለፈው አመት የመጨረሻ ቅዳሜ፡፡ እኛ ስለጎደልን በአባይ ሙላት አልፈነጥዝም፡፡ ሰላም ስላጣን ለሰላም ላገኘነው ኖቤል በደስታ አልሰክርም፡፡ መቀሌ ስለራቀን ኤርትራ መጣች ብለን አንፈነጥዝም፡፡ የሆነው ብዙ ነው፡፡ ይህንን አመት ዳግም አያምጣብን፡፡

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top