Connect with us

እጅ እነሳለሁ!!

እጅ እነሳለሁ!!
Photo: DireTube

ባህልና ታሪክ

እጅ እነሳለሁ!!

#እጅ_እነሳለሁ!!

(አስራት በጋሻው)

ቦይንግ ሰራሹ ማክስ 737 አውሮፕላን ወድቆ በውስጡ የነበሩት ተሳፋሪዎችና ሠራተኞች በሙሉ ከሞቱ በኃላ እና ቀሪ አውሮፕላኖች በሙሉ ያለ ሥራ ቆመው ባሉበት በሀዘናችን ጊዜ ጭምር የአየር መንገዱ ስራ ለአንድ ቀን እንኳ ሳይቋረጥ ኮሮናን ጭምር ተቋቁመን እሰከ ዛሬዋ እለት ላደረሳችሁን ሰራቸኞች እና የማኔጅመንት አባላት እጅ እነሳለሁ።

የኮሮና ወረርሽኝን በሽታ ተከትሎ በአየር መንገዳችን ላይ የደረሰውን ጉዳት ለማካካስ እንዲቻል የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ጭነት አውሮፕላን ለመቀየር ርብርብ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለታደጋችሁ እንጂነሮች እና የአውሮፕላን ቴክኒሻኖች እንዲሁም አመራሮች እጅ እነሳለሁ።

በእቃ ጭነት ክፍል ውስጥ ተመድባችሁ በበረዶ ክፍልና ውጪ በቀዝቃዛው አየር ውስጥ እና በአድካሚ ስራ ላይ ተሰማርታችሁ ይህን አስቸጋሪ ጊዜ እንድናልፍ ቀን ከለሊት ለደከማችሁ ሰራተኞች እጅ እነሳለሁ። በተለይም የስራ ክፍሉን በብቃት በመምራት የተዋጣለት አመራር ለሰጠኸው ለወጣቱ ስትራቴጂስት ለአቶ ፍጹም አባዲ እጅ እነሳለሁ።

በኮሮና ዘመን ህይወታችሁን አሲይዛችሁ ጉዞ የተስተጓጐለባቸውን መንገደኞች ወደየአገራቸው በማጓጓዝ እንዲሁም የጭነት እቃዎችን በእያንዷንዷ የአፍራሪካ ሀገር እና የአለም ጫፍ ድረስ በመብረር ላደረሳችሁ የአውሮፕላን አብራሪዎች እና በፈገግታችሁና በደንበኛ አያያዝ የተመሰገናችሁ የበረራ አስተናጋጆችና አመራሮች እጅ እነሳለሁ።

በዚህ አስከፊ ወቅት አፈር ልሶ መነሳት እንደሚቻል መንገዱን ላሳያችሁን ላበረታችሁን ችግርን ተቋቁሞ ማለፍን ክፉ ዘመንን የማምለጫ አቋራጭ ዘዴዎችን ላመላከተቻሁን ላሻገራችሁን ቆራጥ ከፍተኛ አመራሮች እጅ እነሳለሁ።

በችግር ጊዜ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ ራእይ እንዲኖረን ሰርተህ ላሳየህን ድካምን ከነፍሬዋ እንድናይ በየጊዜው ለምታትረው የአቪዬሽን ጠቢብ የንግድ ተቋሙ መንፈሳዊ መሪ ና የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረማርያም (ዶክተር) አለም ስለአንተ በመሰከረበት ደረጃ ለመግለጽና ለማመሰገን ቃላት ቢያጥረኝም አጎንብሼ እጅ እነሳለሁ።

ሰራተኛውን ከቤቱ ወደ ስራው ከስራው ወደ ቤቱ በቀንም ሆነ በምሽት በማጓጓዝ ደከመኝ ሰለቸኝን ለማታውቁ የመስሪያ ቤታችን የትራንስፖርት ክፍል ሹፌሮች አስተባባሪዎች እና አመራሮች እጅ እነሳለሁ።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ሰራተኛው በአንድ የስራ መንፈስ ተረጋግቶ እንዲሰራ ለአሉባልታ ሳይጋለጥ ድርጅቱን ለታደጋችሁ የሰራተኛ ማህበር አባላትና አመራሮች እንዲሁም ለማህበሩ መሪ እጅ እነሳለሁ።

የኮሮና በሽታ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ለሰራተኛው ግንዛቤ ከመስጠት ጀምሮ ወቅታዊ መረጃ በማካፈል ከሌላው በተሻለ እንድናውቅ በማስተማር በመመርመር በማከም እና የስነ ልቦና ድጋፍ በማድረግ ለረዳችሁን የሜዲካል ዩኒት ሀኪሞች ነርሶች እና ክፍሉን በበላይነት በመመራት ቀን ከለሊት ቤትሽንና ቤተሰብሽን ትተሽ ለምትደክሚልን እኔም በወገብ ህመም ታምሜ በነበረበት ጊዜ ለሶስት ወራት ድጋፍ በማድረግ ከፈግታሽ ጋር ወደ ሥራ እስክመለስ ድረስ ለረዳሽኝ ዶር ሳባ ፍቅሩ እጅ እነሳለሁ።

የድርጅቱ ሰራተኞች ህግንና ደንብን አክብረው እንዲሰሩ አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ በማስተባበር በማበረታታት አለም የደረሰበትን የስራ አመራር ብቃት በማሳየት የሁሉም የስራ ክፍሎች እንደ አንድ ልብ መክረው እንዲሰሩ ላደረጋችሁ የአስተዳደር ሰራተኞችና የስራ መሪዎች እጅ እነሳለሁ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ ደረጃውን አስጠብቆ እንዲቀጥል ከሌሎች ጋር እኩል እንዲራመድ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ እውቀት ያለው ሰራተኛ እንዲኖር ስልጠና በመስጠት ከአየር መንገዱ ውጪ ላሉ ጭምር በዚህ አስቸጋሪ ወቅት አማራጮችን ሁሉ በመጠቀም ላስተማራችሁን ላሰለጠናችሁን የአቪየሽን አካዳሚ ሰራቸኞች መምህራን እና የሥራ መሪዎች እጅ እነሳለሁ ።

አውሮፕላኖች በጥራት ተጠግነው ደህንነታቸው ተጠብቆ በሰአታቸው ለበረራ ዝግጁ እንዲሆኑ በማድረግ በየእለቱ ከበረራ መልስም ሆነ በየተመደበላችሁ ጊዜ በመጠገን ለተፈለጉበት ጊዜ ደቂቃ ሳታዛንፉ በማድረስ ብቃታችሁን ላሳያችሁንና ላስመሰከራችሁ የአውሮፕላን ጥገና ቴክኒሻኖችና ባለሙያዎችና አመራሮች እጅ እነሳለሁ።

አየር መንገዱ ለመንገደኞቹም ሆነ ለሠራተኞቹ ጥራት ያለው ምግብ በማቅረብ በየእለቱ ትኩስና የጣፈጡ ምግቦችን በማዘጋጀት አዳዲስና በሀገር ውስጥ በተገኙ ጥሬ እቃዎች ፈጠራ በመጨመር ሰራታችሁ ላበላችሁን ድርጅቱንም ከወጪ ለታደጋችሁ የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎች እና አመራሮች እጅ እነሳለሁ።

ዘመኑ የደረሰበትን የመጨረሻ ቴኮኖሎጂ እና እውቀት ተጠቅማችሁ በዘመናዊ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ኮሮናን በጥንቃቄ እንድናልፍ ከእጅ ንኪኪ እና ከመሰብሰብ ርቀን ሥራችን ለደቂቃ ሳይተጓጎል እነድንሠራ አየር መንገዱም ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ መንገደኞች ባሉበት ሆነው ሁሉን እንዲፈጽሙ የሚያስችል ፈጠራ የሰራችሁ ቀላል መንገዶችን ላሳያችሁን ለረዳችሁን የአይቲ ክፍል ባለሙያዎች እና አመራሮች እጅ እነሳለሁ።

በኮሮና ዘመን መንገደኞች አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሱበት ከመኪና ማቆሚያ ጀምሮ በመንገደኞች ማስተናገጃ እና መሳፈሪያ ውስጥ መንገደኞች ከውጭ ሀገር ከገቡ ጀምሮ በማስተባበር በማገዝ ሻንጣቸውን በአግባቡ እንዲያገኙ በመርዳት ንጹህና ምቹ አየር ማረፊያ እንዲሆን ገቢና ወጪ መንንገደኞች በመርዳት ጤናቸው ተጠብቆ እንዲስተናገዱ ከኔ ጋር ለምትደክሙ የአዲስ አበባ ኤሮፖርት ሰራተኞችና አመራሮች እጅ እነሳለሁ።

በኮሮና ወቅት የኤርፖርት ማስፋፊያ ስራ ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል መንገደኞች አዳዲስና ምቹ መስተንግዶ እንዲያገኙ ሰፋፊ ማስተናገጃ ቦታዎች በማዘጋጀት ፕሮጀክቶች በሰአታቸው እንዲጠናቀቁ ቀን ከለሊት ለምትለፋው እንዲሁም በስራ ተነሳሽነት የኢትዮጵያ ኤርፖርቶችን በዋና ስራ አስፈጻሚነት ለምትመራው ታታሪው አለቃዬ አቶ እስክንድር አለሙ እጅ እነሳለሁ ።

ሠራተኞች እና መንገደኞች በዚህ የኮሮና ዘመን የእጅ ንጽህና መጠበቂያ እንዲያገኙ አካባቢያቸው ንጹህ እንዲሆን ቀን ከለሊት ለምትሰሩ የጽዳት ሠራተኞች እንዲሁም መንገደኞች የተመቻቸ ጉዞ እንዲያደርጉ ከጫማ ጽዳት ጀምሮ እጆቻየውን እንዲታጠቡ ሳሙን እና ውሀ በማቅረብ ሳኒታይዘር በመሙላት ለምትደክሙ የጽዳት ሠራተኞች
መንደኞች አረንጓዴ ተክሎችና ንጹህ ስፍራዎች እንዲያዪ ለምትለፉ የክፍሉ ሠራተኞች እና አመራሮች እጅ እነሳለሁ።

የመንገደኞችን ሻንጣ በጥንቃቄ በመጫንና በማውረድ በማጓጓዝ እና በማስረከብ ለደቂቃ እረፍትን ለማታውቁ የሜዳው ንጉሶች የራምፕ ሠራተኞች እጅ እነሳለሁ።

መንገደኞች እንደምዘገባቸው እና እንደፍላጎታቸው እንዲሳፈሩ ሻንጣቸውን በመመዝገብ የመረጡትን ወንበራቸውን አግኝተው ተደስተው እንዲሳፈሩ የጉዞ ሰነዳቸውን በአግባቡ ተመልክተው በሄዱበት በሰላም እንዲያልፉ መደበኛ መንገደኞችን ጨምሮ አረጋውያንን አቅመ ደካሞችን አካል ጉዳተኞችን ህጻናትን ለምታግዙ የመንገደኛ ክፍል ሰራተኞችና የስራ መሪዎች እጅ እነሳለሁ ።

የኮሮና ፈተናን ተቋቁማችሁ የሆቴል አገልግሎት ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ላደረጋችሁ የኢትዮጵያ ስካይ ሆቴል ሰራተኞችና አመራሮች እጅ እነሳለሁ።

በድጋፍ ሰጪነት በደንበኛ አገልግሎትና ሽያጭ በገበያ ጥናት በአለም አቀፍ ጥሪ አገልግሎት በጠቅላላ አገልግሎት በጥገና በሂሳብና ፋይናንስ ቁጥጥርና አመራር በማስታወቂያና ህዝብ ግኑኝነት በጸጥታ ጥበቃና ቁጥጥር እና በሌሎችም እዚህ ባልጠቀስኩት የድርጅቱ የስራ ክፍሎች በሰራተኛነትና በአመራር ላይ ላላችሁ በሙሉ እጅ እነሳለሁ ።

የሀገሬ የንግድ አምባሳደሮች ሆናችሁ አየር መንገዱ የሀገራቱ የሽያጭ ወኪሎች በመሆን በመላው አለም ያላችሁ በአውሮፕላኑ ወንበር ልክ ሸጣችሁ በአውሮፕላኑ የጭነት ልክ ጭነቱን ሞልታችሁ የድርሻችሁን ለምትፈጽሙ ከሀገራችሁ ባህል ጋር በማይመሳሰለው ሀገር ተቀምጣችሁ ከቤተሰባችሁና ከህዝባችሁ ርቃችሁ በአስቸጋሪ አየር ንብረት ውስጥ እየኖራችሁ በቋንቋ ተግባብታችሁ ለአየር መንገዳችሁና ለሀገራችን ለምትሰሩ ለጣብያ ሃላፊዎች የየሀገሩ የሽያጭ ሀላፊዎች ከዋናው መስሪያ ቤት ለሚመሩአችሁ አቶ ለማ ያደቻ እና በንግድ ሥራ አስፈጻሚነት የሚመሩት ኢሳያስ ወልደማርያም
በእናንተ እንድኮራ አድርጋችኋል እና እጅ እነሳለሁ ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአንዲትም ቀን ስራው ሳይስተጓጎል እየበረረ ሀገሪቱ የምትፈልገውን የውጭ ምንዛሪ እንድታገኝ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ላስቻሉ የድርጅቱ የበላይ አመራሮች እጅ እነሳለሁ ።

ብዙ አየር መንገዶች በሙሉና በከፊል ዘግተው ሰራተኛ ሲቀንሱና ሲያሰናብቱ ደመወዝ መክፈል አቅቶአቸው የወር ደመወዝ ሲቀንሱና ሲከለክሉ አንድም ሰራተኛ ሳያሰናብት ሳይቀንስ ደመወዝና ጥቅማጥቅምን በሙሉ እየከፈለ እንዲቀጥል ላስቻሉ እኛ የአየር መንገዱ ሰራተኞች በአለም ፊት ቀና ብለን እንድንሄድ ላስቻሉን ድርጅቱም አስቸጋሪ ጊዜን እንዴት ማለፍ እንደሚቻል ለአፍሪካም ሆነ ለሌላው አለም በምሳሌነት ላሳዩ ለአየር መንገዱ የቦርድ አባላት እና ከፍተኛ አመራሮች እጅ እነሳለሁ።

አሮጌውን እና ክፋውን አመት ስላሻገራችሁን መልካም አዲስ አመት ይሁንላችሁ::
(ነሃሴ 30 ቀን 2012)

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top