Connect with us

ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በመጭው መስከረም ወር ይቀጥላል

ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በመጭው መስከረም ወር ይቀጥላል
Photo: Reuters

ዜና

ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በመጭው መስከረም ወር ይቀጥላል

በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብጽ የሚያድርጉት የሶሰትዮሽ ድርድር የፊታችን መስከረም ወር የሚቀጥል መሆኑ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የዉኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ስብሰባ አካሄዱ።

የሶስቱ ሀገራት የዉኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባካሄዱት ስብሰባ የደቡብ አፍሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረትና የአሜሪካ ተወካዮች እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት የወከላቸው ባለሙያዎች በታዛቢነት መገኘታቸውን የዉኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በስብሰባው ባለፈው አንድ ሣምንት በሀገራቱ ባለሙያዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አሞላል እና ዉኃ አለቃቀቅ ደንብ ላይ ሲከናወን የነበረው የባለሙያዎች ድርድር ሪፖርት መቅረቡን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ የሀገራቱ ባለሙያዎች ከነሐሴ 15 ቀን 2012 ጀምሮ በበይነ መረብ ሰብስባቸውን አካሂደዋል ብሏል።

በቀጣይ የሚኖረውን ሂደት በሚመለከት ሀገራቱ የድርድሩን ሂደት የሚገልጽ ደብዳቤ ለደቡብ አፍሪካዋ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ኅብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት የወቅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ናዴሊ ፓንዶር ለመላክ መስማማታቸውን በመግለጫው ተመልክቷል።

ሱዳን የምትሰጠው ማረጋገጫ የሚጠበቅ ሆኖ የሦስትዮሽ ስብሰባው መስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም ይቀጥላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስቴሩ አስታውቋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top