Connect with us

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ያቀረበችለትን ችግሮችን በጋራ የመፍታት ጥያቄ ችላ ማለት

"የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ያቀረበችለትን ችግሮችን በጋራ የመፍታት ጥያቄ ችላ በማለት በተደጋጋሚ አሳዝኗታል"
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ያቀረበችለትን ችግሮችን በጋራ የመፍታት ጥያቄ ችላ ማለት

“የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ያቀረበችለትን ችግሮችን በጋራ የመፍታት ጥያቄ ችላ በማለት በተደጋጋሚ አሳዝኗታል”

ከወርኀ ሰኔው ጥቃት በፊትም ኾነ በኋላ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎችም ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች፣ በቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ በተደጋጋሚ እየደረሱ የሚገኙ ስልታዊ የኾኑ ግልጽ ተጽዕኖዎች እና ጥቃቶች፣ በዐይነት እና በመጠን እየጨመሩ መጥተዋል፡፡

አብዛኞቹ የክልል መንግሥታት፣ ለውይይት ባሳዩት በጎ ፈቃድ፣ ጥቃቱንና ተጽዕኖውን በተወሰነ ደረጃ ለመግታት ቢቻልም በተለይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የወቅቱ አስተዳደር ግን የቀረበለትን በጋራ ችግሮችን የመፍታት ጥያቄ ችላ በማለት እና ባለመቀበል ቤተ ክርስቲያናችንን በተደጋጋሚ አሳዝኗታል፡፡

በክልሉ የተወሰኑ አህጉረ ስብከት ቅዱስ ሲኖዶስ ያገደው ሕገ ወጥ ቡድን ለቤተ ክርስቲያን በሕግ የተሰጧትን መብቶች ከመጋፋት ጀምሮ የአስተዳደር መዋቅሯን እስከ ማፍረስ የተዳፈረው ክልላዊ መንግሥቱ ለቤተ ክርስቲያን ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠት በሚያሳየው ቸልተኝነት እንደ ኾነ ለመረዳት አያዳግትም፡፡

በመኾኑም፣ የትላንቱን ችግር ለማከም፣ ይልቁንም ነገ በከፋ መልኩ ሊመጣ ያለውን አደጋ ለማስቀረት እንዲቻል፣ በጋራ ከመሥራት ውጪ መፍትሔ የለም ብለን እናምናለን፡፡ ስለዚህ ክልላዊ መንግሥቱ ጥያቄያችንን ተቀብሎ በጋራ ለመሥራት ዝግጁ እንዲኾን ቤተ ክርስቲያናችን አጥብቃ ታሳስባለች፡፡

በ2012 ዓ.ም. መባቻ በአንድ ቀን 97 ዜጎች እና ምእመናን ካለቁበት የወርኀ ጥቅምቱ ጥቃት እንዲሁም የወርኀ ጥር የበዓለ ጥምቀት አከባበር ወቅት ከተፈጸሙ ግድያዎች እና ዘረፋዎች ጀምሮ በልዩ ልዩ የአገራችን አካባቢዎች፣ በቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ እየደረሱ ያሉ ግፎችንና በደሎችን መንግሥት አጣርቶ ለፍርድ እንዲያቀርብ ውጤቱንም በይፋ ለሕዝብ እንዲገልጽ ቤተ ክርስቲያናችን አጥብቃ ትጠይቃለች፡፡

(ከትላንቱ መግለጫ የተወሰደ )

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top