Connect with us

በቄስና በኢማም ሞት ፖለቲካ የሚነግድ ያልሰለጠነ ዘመን፤

በቄስና በኢማም ሞት ፖለቲካ የሚነግድ ያልሰለጠነ ዘመን፤
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

በቄስና በኢማም ሞት ፖለቲካ የሚነግድ ያልሰለጠነ ዘመን፤

በቄስና በኢማም ሞት ፖለቲካ የሚነግድ ያልሰለጠነ ዘመን፤
ለመኾኑ ሰሞኑን እየሆነ ያለው ምንድን ነው?
****
ከስናፍቅሽ አዲስ
ሰባ አመት ፖለቲካ አልሰለጥን ባለባት ሀገር እንደመኖር ሲዖል የለም፤ ያ ትውልድ እንዲያ ተጫርሶ ዛሬ የተረፈው ማን በምን ምክንያት እንደሞተ ለሞቱ ምክንያት ይፈጥራል እንጂ ሞት አልባ ፖለቲካ ልክ እንደሆነ ሲያዜም አይታይም፡፡

ዓለም ሰልጥኖ በጨለማ በምትኖረው ሀገር ዛሬም ምሁሩ ስልጣን ለማትረፍ መስጂድና ቤተክርስቲያን ተወሽቋል፡፡ ከወር በፊት ሰውን በማተቡ በማረድ ኢትዮጵያን ድምጥማጥ አጠፋለሁ ብሎ የሞከረው ቡድን ያሰበው ሳይሳካ ከስሮ አክስሮናል፡፡ አሁን ድግሞ ያ ቡድን ይሁን ሌላ ምንም ባላወቅነውም ምክንያት ኢማሞቹ ሞቱ የሚለውን እየሰማን ነው፡፡

በእምነት አባቶች ህይወት እድልን መሞከር ጠያፍ እንደማይሆንባቸው የስልጣን ጥመኞችን ተግባር ደጋግመን አይተነዋል፤ እንዲህ ያለው ችግር ሲፈጠር የመንግስት ዝምታ ግን ግራ አጋብቶናል፡፡ ኢማሞቹ ዛሬ መሞታቸውን እዚህ መንደር እየሰማን የመንግስት ሚዲያዎቹ ትናንት ወያኔ ያደረገልንን ይተርኩልናል፤

የኢማሞቹ ግድያ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተፈጸመ ነው የሚሉ ቅሬታዎች ቀርበዋል፡፡ ይሄንን በሁለት መልኩ ማየት ይቻል ይሆናል፡፡ ቀዳሚው መንግስት ራሱ የፈለገው ነገር ኖሮ ፈጽሞት ይሆን? ብሎ መብሰክሰክ ነው፡፡

ሌላው ግን ደጋግሞ እድሉን የሚሞክረው ሃይል በመንግስት ጸጥታ ውስጥ ተሰግስጎ በኢማም ሞት ቀሪ እድሉን መሞከር ጀምሮስ ቢሆን? የሚለው ነው፡፡ ይሔኛው ላይሆን የሚችልበት እድል ባይኖርም ተግባሩ ተከታትሎ ሲፈጸም ግን መንግስት እንዴት መንቃት አቃተው የሚለው ጥያቄ ያጭራል፡፡

ክርስቲያኑ ተጠቃሁ ብሎ ሙስሊሙ ላይ እንዲነሳ የተሞከረው ክፉ እድል ጨንግፏል፡፡ ጭንገፋው በቀላሉ የተሳካ ግን አልነበረም በመቶዎች መቶው፣ በሺህዎች ተጎድተው፣ አስር ሺህዎች ኑሯቸው ተመሳቅሎ፣ በሺህ የሚቆጠሩ ቤቶች ተቃጥለው፤ ከተሞች ዶግ አመድ ሆነው ነው፡፡

በተመሳሳይ ሙስሊሙ ተጠቃሁ ብሎ ክርስቲያኑ ላይ እንዲዘምት ንጹህ የእምነት አባቶችን ህይወት በመቅጠፍ የሚሰራው ድራማ ቀጥሏል፡፡ ድራማውን ማክሸፍ የነበረባቸው የመንግስት ሚዲያዎች የከሸፈ ድራማና ከመድረክ የወረደ የህወሃት አጀንዳ ላይ ተጠምደዋል፡፡ በኮንሰርት ስርጭት አብደዋል፡፡ ብሔራዊ መግባባት ብለው ወጥቶ መግባት ብርቅ በሆነባት ሀገር በፈጠራ አጀንዳ ታምሰዋል፡፡ በዚህ ግርግር ያልሰለጠነው ፖለቲካ የሰው ህይወት እየተገበረለት አሁንም የወንበር እድሉን ደጋግሞ ይሞክራል፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top