Connect with us

ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ እንዲህ ሲናገሩ የአማራ ፖለቲከኞች ምን እየሰሩ ይሆን?

ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ እንዲህ ሲናገሩ የአማራ ፖለቲከኞች ምን እየሰሩ ይሆን?
Photo: Social Media

ትንታኔ

ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ እንዲህ ሲናገሩ የአማራ ፖለቲከኞች ምን እየሰሩ ይሆን?

ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ እንዲህ ሲናገሩ የአማራ ፖለቲከኞች ምን እየሰሩ ይሆን?
(ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ)

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ሽመለስ አብዲሳ ባለፈው አመት ባልተሰለፉበት ጦርነት ነፍጠኛው በሰበረን ቦታ ላይ ሰበርነው ሲሉ የድል አጥቢያ አርበኝነታቸውን በአደባባይ ነግረውን እያለ የእኛዎቹ ሰዎች ይህ ምን ማለት ነው ብለው የመጠየቅ ሞራል እንኳ ሳኖራቸው በመቅረቱ የአንድ ሰሞን ወሬ ብቻ ሆኖ ቀረ፣ ዶ/ር አብይም ቢሆኑ በተዘዋዋሪ አይዞህ ከማለት ያለፈ ይኸ እንኳ ተገቢ/ነውር አይደለም አላሉም፡፡

ይባስ ብለው አሁን ደግሞ አማርኛ እየሞተ ነው፣ ይህን ለማድረግም አስበን እየሰራን ነው፣ በተቃራኒው ኦሮምኛ እያደገና እየተስፋፋ ነው ሲሉ አማራና አማርኛ ላይ ያላቸውን የመረረ ጥላቻ በግልጽ ነገሩን፣ ብልጽግናን ሲመሰርቱም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም አስበን ሳይሆን ለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም መረጋገጥ በማለም ነው አሉን፡፡ ይህንን ያልተገባ ንግግር ሰምተው የእኛዎቹ ሰዎች ምን እያደረጉ እንደሆነ ያወቅነው የለም፡፡

ከዛም አልፈው ብታምኑም ባታምኑም ሁሉም ክልሎች በፍጥነት ቁልቁል እየሄዱ ነው። ኦሮሚያ ግን ከግምታችሁ በላይ እያደገች ነው። እኛ ምን እየሰራን እንደሆነ አስቀድመው ያወቁት ያለ እረፍት 24 ሰዓት እየጮሁ ነው። እናንተ ግን ገና አልገባችሁም በማለት በኦሮሚያ አመራር አማካኝነት የታቀደውን ሀገር የማፍረስ ሴራ የኦሮሞ ምሁራን እስካሁን ድረስ አለማወቃቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡

በዚህ ረገድ በአንድ ወቅት የቀድሞው የኦነግ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳዮች አማካሪ ኦቦ ሌንጮ ባቲ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያን ዲኮንስትራክት ስናደርግ ቆይተናል፣ ከአሁን ስአት ጀምረን ደግሞ የኦሮሞን ጥቅም በሚያስከብር አኳኋን ኢትዮጵያን ሪኮንስትራክት ለማድረግ እየሰራን ነው ብለውን ነበር፡፡ የአሁኑ የኦቦ ሽመልስ ንግግርም ያስረገጠው ይህንን እውነታ ነው፡፡

ኦቦ ሽመልስም ቢሆኑ እየነገሩን ያለው ይኸውን የተቀናጀ እቅድ መሆኑ ነው፣ ይህን ለማድረግ ደግሞ የነፍጠኛና የትምክህት ማዕከል ነች የሚሏትን አዲስ አበባ ዋጋ አልባ ማድረግ ዋነኛ የትግል ስልታቸው እንደሀነም አሳውቀውናል፡፡ በዚህም መሰረት ቀደም ሲል ኦቦ ለማ መገርሳ በግልጽ እንደተናገሩት፡-

1. የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ ለመቀየር ወደ አዲስ አበባ ኦሮሞዎችን ህጋዊና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በማስገባት የአዲስ አበባን ህዝብ ቁጥር የመቀየር ስራ አንዱ ነው ብለዋል:: ይህም ማለት አሁን ላይ ያለውን የኦሮሞ ቁጥር ከ19.5 ፐርሰንት ከ50 በመቶ በላይ እንዲሆን ማድረግና የአማራን ደግሞ ከ60 ፐርሰንት ቁልቁል እንዲወርድ መስራት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ይሆናል፡፡

2. አዲስ አበባን በአሁኑ ስዓት ያላትን የፓለቲካ: የኢኮኖሚና የባህል ማዕከልነቷን እንድታጣ በማድረግ ጥቅም አልባ ከተማ እንድትሆን ማድረግ፣ ማለትም አዲስ አበባ ከተማ በኢትዮጵያ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ ኢሬለቫንት እንደትሆን ትደረጋለች:: ይህን ለማድረግ ደግሞ ከሚቀጥለው ምርጫ በኃላ የተለያዮ የፌደራል ከተሞችን በመመስረት አዲስ አበባን የፓለቲካና የኢኮኖሚ ማዕከልነቷን ማሳጣት የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ስራ መሆኑም ተገልጧል::

3. ለሌሎች ክልል ህዝቦችም ያዘንን መስለን በመቅረብ የፌዴራሉ ቋንቋ አምስት እንዲሆን ማድረግ ነው፣ እናም አሁን ላይ ያለውን የአማራና የትግራይን የበላይነት በማስወገድ የኦሮሞ ቋንቋን ማስፋፋት ይኖርብናል፣ ይህን ለማድረግ ደግሞ በብልጽግና ውስጥ 40 በመቶ የሚሆነውን ድምጽ እኛ ስለምንይዝ ፕሬዚዳንቱን ለመምረጥ ብቻ ሳይሆን ምክትሉን እንኳ ለመምረጥ የእኛ ድጋፍ ወሳኝ ነው፡፡ ስለሆነም ይህንን አቅማችንን በመጠቀም ኦሮሞ ይበልጥ ተጠቃሚ የሚሆንበት ኢትዮጵያን መፍጠር፡፡

የሚሉት የትግል ስልቶች ተቀምረው ስራ ላይ እንደሚውሉ በግልጽ የነገሩን ሲሆን የእኛዎቹ ፖለቲከኞች ግን ያው በተለመደው መልኩ አሸናፊ ለሆነ ቡድን ሰጥ ለጥ ብለው በመላላክ ለማገልገል ራሳቸውን ያዘጋጁ ይመስላሉ፡፡ ፈጣሪ ልቦና ይስጣቸውና ከእንቅልፋቸው ይንቁ ከማለት ውጭ ሌላ ምን ይባላል!

Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top