የኦሮምያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከወራቶች በፊት በተደረገ ስብሰባ ላይ የተናገሩትን እዚሁ ሰፈር እየተዘዋወረ ይገኛል።
ሰውየው ግልፅ ካደረጓቸው ጉዳዮች አንዱ የቄሮ አደረጃጀት ነው። አደራጆቹና ስምሪት ሰጪዎቹ እኛ ነን ብለዋል።
አዲስአበባ ላይ እያስፈፀሙ ያሉት እንዲሁም ቋንቋን በተመለከተ የሰሩትን ተናግረዋል።
በነገራችን ላይ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በመሾም ቃለመሀላ የፈፀሙት የካቲት 11ቀን 2012 ዓ.ም ነበር። ከዝያ በፊት በሚያዚያ ወር 2011 ዓ.ም ጨፌ ኦሮምያ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ተሹመው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ይኸን የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ንግግር እርስዎ እንዴት አገኙት? ከስድብና ዘለፋ የፀዳ አስተያየት ቢሰጡን?
ከአቶ ሽመልስ ንግግር ጥቂት ነጥቦች እነሆ።
***
~ “አንድ ነገር ልንገራችሁ አማራ ቁልቁል እየሄደ ነው። አማራ እየሞተ ነው። አማራ ስል አማርኛን ነው ብሔሩን አይደለም። አደራችሁን ይሄ ውጭ አይወራም ። ”
~ “ዘመድ ለማፍራት ብዙ ተሰርቷል። ……አባይን ተሻግረን ባህርዳር ብዙ ሰርተናል። የቻልነውን አሳምነን (Convince) ያልቻልነውን ግራ አጋብተን (Confuse) ። አሁን የሚያስቸግረው ሌሎች ለምን ግራ ተጋቡ ብላችሁ ትጨነቃላችሁ። ምን አገባችሁ?”
~“ብትወዱም ባትወዱም ቄሮን የፈጠረው ኦህዴድ ነው። ሰልፍ ስናስወጣም ስንበትንም የነበርን እኛ ነን።”
~ቁማር በደንብ ነው የተጫወትነው። ቁማሩን ስለተጫወትን ነው የበላነው። …ፖለቲካ ተንኮል ነው። ከውስጡ ሌላ የለውም። ምን ያህል ተንኮል ትችላለህ ነው ዋናው።”
~ ከአሁን በኋላ ብልፅግናን የሚመራው ኦሮሞ ወይንም ኦሮሞ የፈቀደለት ብቻ ነው። TPLF ኦህዴድን የፈጠረው ለኦሮሞ ህዝብ ብሎ ሳይሆን ለራሱ ነው። እኛም ብልፅግናን የፈጠርነው ለኛ እንደሚመችን አድርገን ነው። ብልፅግናን የፈጠርነው ከስልጣን ለመውረድ አይደለም።
~ ለአዲስ አበባ ብዙ መፍትሔ አለ። አንደኛው በሕገወጥም ሆነ በህጋዊ መንገድ ሰው ማስገባት ነው። ሌላኛው አዲስ አበባን የማትጠቅም ከተማ ማድረግ ነው። በኢኮኖሚ እናዳክማታለን። ከተሳካልን የፌደራል መንግስት መቀመጫነቷን ሦስት እና አራት ቦታ እንሰነጥቀዋለን ። የድንበር መካለያ አዋጁ ወጥቷል። እሱ ለስሙ ይፀድቃል። ዋናው ግን አዋጁ አይደለም። እኛ በአጭር ጊዜ ዴሞግራፊውን ለመቀየር እየሰራን ነው ”