Connect with us

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የአፍሪካ ከፍተኛውን የስፖርት ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የአፍሪካ ከፍተኛውን የስፖርት ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
Photo: Social Media

ስፖርት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የአፍሪካ ከፍተኛውን የስፖርት ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ የአፍሪካ ብሄራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር /አኖካ/ ለኦሎምፒክ ስፖርት ዕድገት ድጋፍ ላደረጉ መሪዎች እና ታዋቂ ሰዎች የሚሰጠው ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ተገልጿል።

ለኢትዮጵያ ስፖርት እና ለኦሎምፒክ ንቅናቄ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ነው በአፍሪካ በስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የሆነው ሽልማት ተሸላሚ መሆናቸውን አኖካ ያስታወቀው።

ማኅበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ በቀጣይ በሚመረጥ ቦታና ጊዜ ሽልማቱ እንደሚበረከትላቸው አስታውቋል ሲል ፋብኮ ዘግቧል።

ዘንድሮ ሊካሄድ የነበረውን የቶክዮ ኦሎምፒክን መሰረት በማድረግ ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝ ከመከሰቱ ቀደም ብላ ባሉት ወራት ሰፊ ከማስ ስፖርት ጋር በማስተሳሰር ሀገር አቀፍ የኦሎምፒክ ስፖርት ንቅናቄ ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል።

Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top