Connect with us

” ገንቢዎች እንጂ አውዳሚዎች አትሁኑ!…. “

" ገንቢዎች እንጂ አውዳሚዎች አትሁኑ!.... "
President Barack Obama presents a 2010 Presidential Medal of Freedom to Rep. John Lewis, D-Ga., Tuesday, Feb. 15, 2011, during a ceremony in the East Room of the White House in Washington.Carolyn Kaster / AP, file

ባህልና ታሪክ

” ገንቢዎች እንጂ አውዳሚዎች አትሁኑ!…. “

” ገንቢዎች እንጂ አውዳሚዎች አትሁኑ!…. ”

(ታምሩ ገዳ)

“ብጥብጥ የትግል ስልት አይደለም፣ ብጥብጥ የሰላማዊ እምቢተኝነት አካል አይደለም፣ እኔ እንደማስበው ብጥብጥ አንዳንድ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ በሌሎች ሰዎች ላይ የሚከተሉት የጥቃት፣ የንብረት ውድመት ፍልስፍና ውጤት ነው። ከብጥብጥ የሚገኝ አንዳች አዎንታዊ ፋይዳ የለም። ብጥብጥ ከውስጥ ፈንቅሎ የሚወጣ የጥፋት ድርጊት ነጻብራቅ ነው። ”

“መሳሪያ ያልያዙ ሰዎች ያለወንጀላቸው ሲታሰሩ፣ሲደበደቡ፣ሲገደሉ ማየት በእጅጉ ያመኛል። ሰለ እነርሱ ስለቤተሰቦቻቸው፣ ሰለ አገራችንም ልቤ ክፉኛ ይነካል። ህመማችሁን፣ ተስፋ መቁረጣችሁን እመለከታለሁ፣ አዳምጣለሁ ። ነገር ግን ብጥብጥ ዝርፊያ እና ንብረት ማውደም በምንም መልኩ የህዝባዊ ተቃውሞ እና የሰላማዊ እምቢተኝነት ታክቲክ ሊሆን አይችልም። ከአስር አመታት በፊት ስለ እኩልነት እና ስለፍትህ ለመጮህ ወደ አደባባይ ስንወጣ ዘር፣ ቀለም፣ ጾታ፣ ሀይማኖት አልገደበንም ነበር።

ዛሬም የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ለተቃውሞ ወደ ጎዳናዎች የምትወጡ ያገሬ ልጆች እኛ የተጓዝንበትን የሰላማዊ መንገድ እና ታክቲክን ተከተሉ፤ ገንቢዎች እንጂ አውዳሚዎች አትሁኑ።”

ታሪክ ደግሞ ደጋግሞ እንዳስተማረን እና እንዳረጋገጠልን ከምንፈልገው የስኬት ማማ ላይ ለመውጣት ብቸኛው መፍትሔ ብጥብጥ፣ ዝርፊያ እና ውድመት ሳይሆን ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው።”

(እድሜ ልካቸውን ሰለተገፉ ወገኖቻቸው መብት ሲታገሉ ቆይተው ትላንት በሰማኒያ አመታቸው የቀብር ስነስርአታቸው የተፈጸመው አሜሪካዊው የመብት ተሟጋች እና የህዝብ እንደራሴው ጆን ሉዊስ በተለያዩ ጊዜያት ከሰጡት ምክሮች የተወሰደ)

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top