Connect with us

በቤንሻንጉሉ ጥቃት የህውሓት እጅ አለበት

በቤንሻንጉሉ ጥቃት የህውሓት እጅ አለበት
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

በቤንሻንጉሉ ጥቃት የህውሓት እጅ አለበት

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ያደረሰው ታጣቂ ኃይል በህውሓት ስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያገኙ የአማራ ክልል አስታወቀ። ዓላማው በብሄር ብህረሰቦች መካከል ግጭት በመፍጠር የአካባቢውን ሰላም ለማወክ መሆኑም ተመለከተ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈትቤት ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር በጥቃቱ ዙሪያ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ጥቃቱን የፈጸመው ኃይል በአካባቢው የብሔር ግጭት የመቀስቀስ ዓላማ በመያዝ ተደጋጋሚ የጥፋት ሙከራ ሲያደርግ የቆየ ነው።

ታጣቂ ኃይሉ በህውሓት የስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግለት አመልክተው፤ ህውሓት ሀገርን ለማተራመስ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ አካል መሆኑምን ጠቁመዋል። ድርጊቱ ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ አጥፊዎችን ፈልጎ ለመያዝና አስፈላጊውን ዕርምጃ ለመውሰድ የፀጥታ መዋቅሩ የተጠናከረ ጥረት እያደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል ።በአሁኑ ጊዜም አካባቢው ላይ ሰላም ሰፍኗል።አርሶአደሩም የእርሻ ሥራውን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል፡

ችግሩ የደረሰበት አካባቢ የአማራ ክልል አርሶአደሮች በስፋት የእርሻ ሥራ የሚያከናውኑበትና በቀን ሥራም ተቀጥረው የሚሠሩበት እንደሆነ የጠቆሙት አቶ አገኘሁ፤ በአማራ እና በጉሙዝ ብሄረሰብ መካከል ምንም ዓይነት ግጭት እንደሌለና ለዘመናት አብሮ የኖረ ህዝብ መሆኑም አስረድተዋል፡፡

ድርጊቱ በሰላም አብሮ የኖረውን ህዝብ ለማለያየት ሆን ተብሎ የተፈጸመ መሆኑንም አመልክተዋል።ማን እንደፈጸመውም ይታወቃልም።አጥፊውን ታጣቂ ኃይል ህወሓት በገንዘብና በሥልጠና እንደሚያግዘውም አመልክተዋል፡፡

ጥቃቱ ህውሓት ለውጡን ወደቀውስ ለመለወጥ ምን ያህል አልሞ እየሠራ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ያሉት ኃላፊው፤ ለህብረተሰቡ በችግሩ ዙሪያ ግንዛቤ በማስጨበጥ ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ የማድረግ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ጠቁመዋል።በዚህም እስከአሁንም በአማራ ክልል የሽብር ተግባር ለማከናወን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ95 በላይ ፀጉረ ልውጥ ሰዎችን መያዛቸውን አመልክተዋል፡፡

በአጥፊ ታጣቂ ኃይል ሕይወታቸው ያለፈ የአማራ ክልል አርሶአደሮች 12ቱ ከምዕራብ ጎጃም፣ ሁለቱ ደግሞ ከጎንደር መሆናቸውንና የሁሉም አስክሬን ለቤተሰብ ተሰጥቶ በክብር የቀብራቸው ሥነሥርዓት መፈጸሙን ገልጸዋል።አርሶአደሩ በተፈጸመው ነገር ሳይደናገጥ የወቅቱን የእርሻ ሥራ እንዲያከናውንም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱላዚዝ መሀመድ በመተከልዞን ጉባ ወረዳ ከሀገር ውጭና ከውስጥ ተልዕኮ የተሰጣቸው የጥፋት ኃይሎች ሐምሌ 20 ቀን 2012 ምሽት አካባቢ አቡጃር ቀበሌ ባደረሱት ጥቃት የ14 ንጹሐን ዜጎች ሕይወት ማለፉን ከትናንት በስቲያ ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡

በወቅቱም የጥፋት ቡድኑ ተገቢ ስልጠናና ተልዕኮ በመያዝና በከባድ መሳሪያ በመታገዝ በተለይም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት የማስተጓጎል እና የብሔር ግጭት የመቀሳቀስ ዓላማ በመያዝ ተደጋጋሚ የጥፋት ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡

የክልሉ የጸጥታ ኃይል ከመከላከያ ሠራዊትና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን ቀደም ብሎ በአካባቢው ሠላምን ለማረጋገጥ ዕርምጃ ሲወስድ መቆየቱን አመልክተዋል። በጥፋት ቡድኑ ላይ እየተወሰደ ካለው ዕርምጃ በተጨማሪ አራት ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመዋል። ሕግን የማስከበር ዕርምጃዎች በአካባቢው ተጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቀዋል፡፡

(አዲስ ዘመን ሐምሌ 23/2012)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top