Connect with us

የድርድሩ መሰረዝና የግብፁ ፕሬዝደንት አስተያየት

የድርድሩ መሰረዝና የግብፁ ፕሬዝደንት አስተያየት
Photo: daily news egypt

ዜና

የድርድሩ መሰረዝና የግብፁ ፕሬዝደንት አስተያየት

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ በምታስገነባዉ ግድብ ሰበብ የሚወዛገቡት የኢትዮጵያ፣የሱዳንና የግብፅ የዉኃ ባለስልጣናት ትናንት የጀመሩትን ድርድር ወዲያዉ አቋረጡ። በሌላ ዜና የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታሕ አል ሲሲ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ስለምታስገነባዉ ግድብ የሚደረገዉ ድርድር ትዕግስትን የሚጠይቅ ግን ተስፋ የሚጣልበት እንደሆነ አስታወቁ።

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ በምታስገነባዉ ግድብ ሰበብ የሚወዛገቡት የኢትዮጵያ፣የሱዳንና የግብፅ የዉኃ ባለስልጣናት ትናንት የጀመሩትን ድርድር ወዲያዉ አቋረጡ። የጀርመኑ ዜና ወኪል DPA እንደዘገበዉ የአፍሪቃ ሕብረት በያዘዉ ቀጠሮ መሠረት የሶስቱ ሐገራት የዉሐ ሚንስትሮች ትናንት በኢንተርኔት መወያየት ነበረባቸዉ።ይሁንና የሱዳኑ የዉኃና የመስኖ ሚንስትር ያሲር አባስ ለእያንዳዱ የድርድር ወቅት ግልፅ የመነጋገሪያ ርዕሥ ወይም አጀንዳ መቀረፅ አለበት በሚል የትናንቱ ድርድር እንዲቋረጥ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚወዛገቡት ሶስቱ ሐገራት ለአስር ዓመታት ያሕል ቢደራደሩም እስካሁን አግባቢ ስምምነት ላይ አልደረሱም።ድርድሩ የሚቀጥልበት ዕለትንም የጀርመኑ ዜና ወኪል አልጠቀሰም።የብሪታንያዉ ዜና ወኪል ሮይተር እንደዘገበዉ ደግሞ ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመጀመሪያ ዙር ዉኃ መሙላትዋን ሱዳንና ግብፅ ተቃዉመዋል።የሁለቱ ሐገራት ባለስልጣናት እንደሚሉት ኢትዮጵያ፣ ሶስቱ ሐገራት ሳይስማሙ ግድቡን መሙላትዋ ድርድሩን አጠራጣሪ ያደርገዋል።ኢትዮጵያ የመጀመሪያዉን ዙር የዉኃ ሙሌት ማጠናቀቅዋን ያረጋገጠችዉ ባለፈዉ ሳምት ነበር።

በሌላ ዜና የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታሕ አል ሲሲ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ስለምታስገነባዉ ግድብ የሚደረገዉ ድርድር ትዕግስትን የሚጠይቅ ግን ተስፋ የሚጣልበት እንደሆነ አስታወቁ።አል ሲሲ ምስራቃዊ ካይሮ ዉስጥ የተገነባ የኢንዱስትሪ ፓርክ መርቀዉ ሲከፍቱ እንዳሉት ድርድሩ በየሰበብ አስባቡ ረጅም ጊዜ መዉሰዱ አይቅርም።ይሁንና አክለዉ እንዳሉት ዉዝግቡ በድርድር ይፈታል የሚል ተስፋም አላቸዉ «እየተደራደርን ነዉ።» አሉ የቀድሞዉ ጄኔራል፤ መንግስታቸዉ በሚቆጣጠረዉ ቴሌቪዥን ጣቢያ በተሰራጨ መልዕክታቸዉ፣ «ድርድሮቹ የረጅም ጊዜ ፍልሚያን ይጠይቃሉ—-ግን በፈጣሪ ፈቃድ ለዉጤት እንበቃለን» ቀጠሉ።መገናኛ ዘዴዎች «የጦርነት አደጋ እንዳለ አድርገዉ» ከመዘገብ እንዲታቀቡም አል ሲሲ አሳስበዋል። #DW

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top