Connect with us

ሸገር የዳቦ ፋብሪካ በግማሽ አቅሙ እያመረተ ነው

ሸገር የዳቦ ፋብሪካ በግማሽ አቅሙ እያመረተ ነው
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

ሸገር የዳቦ ፋብሪካ በግማሽ አቅሙ እያመረተ ነው

በተመጣጠነ ዋጋ ዳቦ ለኅብረተሰቡ ለማቅረብ እንዲችል ታስቦበት ሥራ የጀመረው ይህ ፋብሪካ በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ ያመርታል በሚል ነበር፡፡

ባለፈው ሰኔ ወር ተመርቆ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ የሚገኘው ፋብሪካው በአሁኑ ሰዓት የታሰበውን ያክል እያመረተ ይሆን? ስንል ጠይቀናል።

የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ሃይሉ ቡልቡላ እንደነገሩን ፋብሪካው በሰዓት 80 ሺህ የማምረት አቅም ቢኖርም በአሁኑ ሰዓት እያመረተ ያለው ግን በሰዓት ከ30-35 ሺህ ነው ብለዋል፡፡

ፋብሪካው አሁን ላይ በቀን 700 ሺህ ገደማ ዳቦ በማምረት ላይ መሆኑንም ነግረውናል።

የምርት ሂደቱ የታሰበውን ያክል በፍጥነት ያልሄደበት ምክንያት ለምድን ነው? ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ የኮሚሽን ስራዎች ባለመጠናቀቃቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በቅርቡም ከውጪ በሚገቡ ባለሙያዎች አማካኝነት ይህንን ሂደት ለማጠናቀቅ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውና ይህ ሲጠናቀቅ ፋብሪካውም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ስራ እንደሚገባ ነግረውናል፡፡

ይህ እንዳለ ሆኖ ግን የሸገር ዳቦ በሚሰራጭባቸው የመሸጫ ሱቆች ከነዋሪዎች ውጪ ዳቦ ቸርቻሪዎች በዝቅተኛ ዋጋ ገዝተው ዋጋ ጨምረው የሚሸጡ ነጋዴዎች እንዳሉ አስተያየታቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም የሰጡ ሸማቾች ተናግረዋል።

(ኢትዮ ኤፍ ኤም)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top