Connect with us

የትግራይ ህዝብ የህወኃትን የግፍ አገዛዝ በቃህ ሊለው ይገባል- የብልጽግና ፓርቲ

የትግራይ ህዝብ የህወኃትን የግፍ አገዛዝ በቃህ ሊለው ይገባል- የብልጽግና ፓርቲ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

የትግራይ ህዝብ የህወኃትን የግፍ አገዛዝ በቃህ ሊለው ይገባል- የብልጽግና ፓርቲ

የትግራይ ህዝብ የህወኃትን የግፍ አገዛዝ በቃህ ሊለው ይገባል- የብልጽግና ፓርቲ

የትግራይ ህዝብ የህዝባዊ ወያኔ ኃርነት ተግራይ (ህወኃት)ን የግፍ አገዛዝ በቃህ ሊለው እንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ። ፓርቲው በክልሉ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ጭቆና እና አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏልም ብለዋል። የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ አመራር የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ‘የብልጽግና ፓርቲ አጠቃላይ አቅጣጫን የሚያሳይ ሰነድ’ ላይ ውይይት አድርገዋል።

አመራሮቹ በነበራቸው ውይይት ህዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትግራይ (ህወኃት) አሁንም ከፍተኛ ግፍና በደል እየፈጸመ የሚገኝ ድርጅት ነው ብለዋል። በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ጭቆና መንሰራፋቱን የተናገሩት አባላቱ በተለይ በራያና ሌሎች አካባቢዎችም ከባድ በደል እየተፈጸመ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለመደመር ምሳሌ የሚሆነው የትግራይ ሕዝብ ይህን ጨቋኝ ቡድን መታገል ይኖርበታልም ነው ያሉት። መንግስትም ቢሆን ህወኃት በሕዝቡ ላይ በይፋ እየደረሰ ያለውን አፈና እና ጭቆና ሊያስቆም ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል።

ከምንም በላይ ሚዛናዊ የሆኑ የፖለቲካ ሊሂቃንን እንዲሳተፉ በማድርግ የትግራይ ሕዝብ ራሱን ከህወኃት አፈና በማላቀቅ ፖለቲካዊ ተሳትፎውን ማረጋገጥ ይኖርበታል ነው ያሉት። የህወኃት ሊሂቃን የትግራይን ህዝብ መረማመጃ በማድረግ ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ቆመው የኖሩ መሆናቸውን ያስታወሱት የብልፅግና አመራሮች ህዝቡ ከዚህ በኋላ ሊሸከማቸው አይገባም ብለዋል።

ህወኃት በትግራይ ክልል አካሂዳለሁ ለሚለው ምርጫ ነገሩ ወደ ባሰ ሁኔታ ሳያመራ ከወዲሁ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባም አሳስበዋል።
ከትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ዶክተር አብረሃም በላይ እንደተናገሩት ብልጽግና ችግሮችን ለማስወገድ ሲል በመፍትሄዎች ላይ አተኩሮ ይሰራል።

ህወኃት ሕገ መንግስትን ጭምር የሚጥስ ተግባራትን ሲያከናውን ብልፅግና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየታጋለ መሆኑንም ገልጸዋል። ህወኃት ከዚህ በኋላ ተቀባይነት እያጣ በመሆኑ በምርጫ ሰበብ ሕዝቡን ለማደናገር አስቦ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
የትግራይ ሕዝብ የህወኃትን ሴራ በቅጡ በመረዳት ሊታገለው ይገባልም ብለዋል።

የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጂጌ በበኩላቸው የትግራይ ሕዝብ የሚሻለውን እያገናዘበ የሚሄድ አስተዋይ ህዝብ መሆኑን ጠቅሰዋል። የትግራይ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ሁለንተና ትልቅ ሚና የተጫወተ ታላቅ ሕዝብ ሲሆን ለውጥ ፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።

እንደ አቶ ተስፋዬ ገለጻ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የፖለቲካ ድርጅትና ሕዝብን አንድ አድርጎ ማቅረብ ተገቢ አለመሆኑንም አስረድተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችም ፓርቲው ለእውነተኛ ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት የተዘጋጀ መሆኑን ማስረዳት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ህወኃት ምርጫ ማስፈጸም የፌደራል መንግስት ስራ መሆኑን እያወቀ ሕገ መንግስታዊ አሰራሩን ለመጣስ መዘጋጀቱ አይጠቅመውም ሲሉም ተናግረዋል።

የፌዴራል መንግስት ከህወኃት ጋር ወደ ጦርነት የሚገባበት ምንም ምክንያት የለውም ሲሉም አስረግጠዋል። የብልጽግና አመራሮች በቀጣዮቹ ወራት የታቀዱትን የክረምት ስራዎች በከፍተኛ ተነሳሽነት እንዲፈጽሙም አሳስበዋል።
ምንጭ- ኢዜአ

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top