Connect with us

ኢትዮጵያ በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ ታጣለች ተባለ

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ኢትዮጵያ በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ ታጣለች ተባለ

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በሀገሪቷ በተቀሰቀስው አለመረጋጋት ምክንያት የሀሰት መረጃዎችንና ብጥብጥ ሊያስነሱ የሚችሉ መልዕክቶችን ለመቆጣጠር ሙሉ ለሙሉ ኢንተርኔት መዘጋቱ የሚታወስ ሲሆን በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ ከ3.5 ቢሊዮን ብር እንዳጣች “NetBlocks” የተባለው አለም አቀፍ የኢንተርኔት ነፃነት የሚቆጣጥር የሲቪል ማህበረሰብ ተቋም ለዴይሊ ኔሽን ተናግሯል።

የተቋሙ ዳይሬክተር Alp Toker እንደገለፁት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሀገሪቷ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና የሚያሳድር መሆኑን ገልፀዋል። ተቋሙ በሚጠቀምበት ኮስት ኦፍ ሸትዳውን (COST) በተባለ የመለኪያ ሞዴል በተሰራው ቀመር በመዘጋቱ ብቻ በየቀኑ ከ 150 ሚሊዮን ብር በላይ እያጣች እንደነበር ተብራርቷል።

ኮስት ኦፍ ሸትዳውን (COST) በዚሁ ተቋም ተዘጋጅቶ የቴሌኮሚኒኬሽን ኢንዱስትሪንና የሀገር እድገት ጠቋሚ መረጃዎችን በማጣመር ኢንተርኔት በሚቋረጥበት አካባቢዎች የደረሱ ጉዳቶችን የሚያብራራ መገልገያ ነው።

ኢትዮጵያ ከ23 ቀናት በኃላ ባሳለፍነው ሀሙስ ሙሉ ለሙሉ በመላው ሀገሪቷ የኢንተርኔት አገልግሎትን መልቀቋ የሚታወስ ሲሆን መንግስት በበኩል በዚህ ቀናቶች  ሁከቱን ለመቆጣጠር ከፍተኛ እገዛ እንዳደረገለት ተናግሯል።

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top