Connect with us

ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ የመንግስት ተሿሚዎች ስም ዝርዝር ለህዝብ ይፋ ያደረጋል ተባለ

ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ የመንግስት ተሿሚዎች ስም ዝርዝር ለህዝብ ይፋ ያደረጋል ተባለ
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ የመንግስት ተሿሚዎች ስም ዝርዝር ለህዝብ ይፋ ያደረጋል ተባለ

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 90 በመቶ የሚሆኑ የመንግስት ተሿሚዎች ፣ የህዝብ ተመራጮች እና ሌሎች የሀብት ምዝገባዉ የሚመለከታቸዉ አካላት ሀብትና የገቢ ምንጭ ማስመዝገባቸውን አስታውቋል፡፡

በኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መስፍን በላይነህ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የ84 ሺህ 460 ሀብት አስመዝጋቢዎችን ሀብትና የገቢ ምንጭ ለመመዝገብ ታቅዶ ይገኛል፡፡

ኮሚሽኑ የሀብት ምዝገባዉ መጠናቀቂያ ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ መሆኑን ገልፃ የነበረ ቢሆንም ፤ በሀገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት ሀብታቸውን ማስመዝገብ ያልቻሉ አካላት አስከ ሀምሌ 30 ቀን 2012 መራዘሙን ይፋ አድርጓል፡፡

በነዚህ ቀሪ ቀናቶች ምዝገባውን ያልከወኑ 10 በመቶ የመንግስት ተሿሚዎች ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

አንደ አቶ ተስፋዬ ማብራሪያ እነዚህ ተሿሚዎች በስምም ሆነ በተቋማቸው የተለዩ በመሆናቸው ደብዳቤ እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡ ይህንኑ በመገዘብ በቀሩት አጭር ቀናት ውስጥ ሀብታቸውን የማያስመዘግቡ ከሆነ ኮሚሽኑ ስም እየተጠቀሰ ለህዝብ ይፋ ያደረጋል ብለዋል፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top