Connect with us

“ከሽፏል” ~ አቶ ሺመልስ አብዲሳ

"ከሽፏል" ~ አቶ ሺመልስ አብዲሳ
Photo: Facebook

ዜና

“ከሽፏል” ~ አቶ ሺመልስ አብዲሳ

“ከሽፏል” ~ አቶ ሺመልስ አብዲሳ
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት

መንግስት በሆደ ሰፊነት ዴሞክራሲን ለማስፋት የፈጠረውን የፖለቲካ ምህዳር እንደፍርሃት የቆጠሩ አካላት መንግስትና ህዝብን ለመበተን ያደረጉት ጥረት በፀጥታ አካላትና በህዝቡ ርብርብ ሊከሽፍ መቻሉን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡

ጨፌ ኦሮሚያ 12ኛ መደበኛ፣ 5ኛ ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሲነዙ የነበሩ የውሸት ፕሮፓጋንዳዎች ፍሬአልባ ሆነው አሁን ላይ ግድብ የመጀመሪያ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት ማሳካት መቻሉን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ ለጨፌ አሮሚያ ባደረጉት ንግግር ላይ አንስተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱም በኢኮኖሚ ዘርፍ አበረታች ውጤቶች ቢመዘገቡም ኮቪድ-19 እና የፀጥታ ችግሮች የታሰበውን ያህል እንዲሳካ አላደረጉም ብለዋል አቶ ሺመልስ፡፡

ሆኖም አሁንም በዘርፉ ወደፊት ለመሄድ የሚያስችል መልካም አጋጣሚ መፈጠሩን ተገልጿል፡፡

ጉባኤው ዛሬ እና ነገ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የሕግ ማርቀቅ እና በተጓደሉ አመራሮች ቦታ ሹመት ያጸድቃል ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡(ETV)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top