Connect with us

‹ጦርነትን እመርጣለሁ› – ናጉቢ ስዋሪስ፤ ግብጻዊ ቢሊየነር

‹ጦርነትን እመርጣለሁ› - ናጉቢ ስዋሪስ ፤ ግብጻዊ ቢሊየነር
Photo: Social Media

ፓለቲካ

‹ጦርነትን እመርጣለሁ› – ናጉቢ ስዋሪስ፤ ግብጻዊ ቢሊየነር

በቴሌኮም፣ በሚዲያ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የተሰማሩት ግብጻዊው ቢሊየነር (ባለሃብት) ናጊቡ ስዋሪስ ( Naguib Sawiris) ከ “ዘ አፍሪካን ሪፖርት” ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ጦርነትን እመርጣለሁ አሉ፡፡ ሰፋ ካለው ቃለምልልሳቸው የህዳሴ ግድብን የሚመለከተው ጉዳይ ብቻ እነሆ ተቀንጭቦ ቀርቧል፡፡

ጥያቄ፡- በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግብፅ ምን መብት አላት?

መልስ፡- ናይል ወደ እኛ ይመጣል ፣ ውሃው የሚመጣው በአራት ወይም በአምስት የአፍሪካ ሀገሮች በኩል ነው – እኛ ከአንዱ ጋር መጥፎ ግንኙነት ካለን የተቀረው ጋር ጥሩ ግንኙነት አለን ፡፡ እናም አፍሪካን ከተመለከቱ ግብፅ የሰሜን ዋልታ ነች በተቃራኒው ደቡብ አፍሪካ ደቡብ ዋልታ ነች።

ጥያቄ፡- በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ሊኖር ስለሚችል ጦርነት ቀደም ብለው ጠቅሰዋል ፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ‹ግብፃውያን በአባይ ወንዝ ላይ መብት አላቸው› የሚል የፒቲሽን ፊርማ ሲሰበሰብ ነበር፡፡ ወታደራዊ እርምጃ የሚቻል ይመስልዎታል? ይህ ምክንያታዊ ነው?

መልስ፡- ምክንያታዊ አይደለም። ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ፡፡ አንድ ሰው ቤትህ ውስጥ ይቆልፍብሃል፡፡ ምግብ የለህም ወይም ምግብ እያጣህ ነው እንበል ፡፡ምን ትሆናለህ? ግብጻውያንም እንዲሁ ናቸው፡፡ በአባይ ወንዝ ላይ መቶ በመቶ ጥገኛ ስለሆኑ ቤት እንደተዘጋበት ሰው ምግብ አይኖራቸውም ፡፡ ስለዚህ በድንገት ሁሉም የእርሻ መሬት ይደርቃል እናም ሰዎች መሞት ይጀምራሉ። ስለዚህ ምን ማድረግ ትችላለህ? ሰዎች ሲሞቱ ዝም ብለህ ብቻ ትመለከታለህ? ወይስ ለእነሱ መብት ትታገላለህ?

ጥያቄ፡- ግን የ1959 የግብፅ እና የ ሱዳን ስምምነት በጣም መጥፎ ስምምነት ነበር

ስለሆነም በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት የምንጀምር ከሆነ ተጠያቂዋ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ምክንያቱም ጥያቄዋ ብዙ ዓመታት ታሪክ መሰረት ያደረገ ነውና፡፡ እኔ በበበኩሌ እንደ አንድ ግብፃዊ ፣ በዙሪያችን ያሉትን ግድግዳዎች የሚዘጉ ከሆነ ጦርነትን እመርጣለሁ ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top