Connect with us

ኢቲቪ እና ኢቢኤስ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ተቀጡ

ኢቲቪ እና ኢቢኤስ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ተቀጡ

ህግና ስርዓት

ኢቲቪ እና ኢቢኤስ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ተቀጡ

– ቅጣቱ ለሚዲያዎች ትልቅ ትምህርት የሚሆን ነው

ከአራት ዓመት በፊት ዙና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሶስት ወራት ውስጥ ሲኖትራክ ገልባጭ መኪና ገዝቶ እንደሚያስረክባቸው በኢቲቪ እና በኢቢኤስ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ባሰራጨው ማስታወቂያ ተታለው ሙሉና ግማሽ ክፍያ በመክፈላቸው መጭበርበራቸውን በግልና በተናጠል አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ ከቆዩ ወገኖች አቤቱታ መረዳት ይቻላል፡፡

አቤቱታ አቅራቢዎቹ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና በኢቢኤስ ቴሌቭዥን ዙና ትሬዲንግ መኪኖችን እንዳስመጣ በማስመሰል ባቀረበው የተተሳተ ማስታወቂያ ተታለው የግዥ ውል መፈጸማቸውን በመናገር በሁለቱ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ላይ ያቀረቡት የፍትሐብሔር ክስ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ጣቢያዎቹ ላይ ውሳኔ በመስጠት ተጠናቅቆ ነበር፡፡ ሆኖም ጣቢያዎቹ በጣምራ ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ፍትሐብሔር ችሎት ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ማጽናቱን የሸገር ራዲዮ ዜና ዘገባ ያስረዳል፡፡

በዚህ መሰረት ኢቲቪ፣ ኢቢኤስ እና ማስታወቂያውን ሰርቶታል የተባለው አቤኔዘር የማስታወቂያ ድርጅት በግልና በጋራ ዙና ትሪዲንግ ሰብስቦታል ከተባለው 58 ሚሊየን ብር አንድ አራተኛውን እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል፡፡

ጣቢያዎቹ ለቅጣት የተዳረጉት የዙና ትሬዲንግን የንግድ ስራ ፈቃድ ብቻ በማየት የሚሰሩትን ማስታወቂያ ትክክለኛነት ሳያረጋግጡ በማሰራጨት ለበርካታ ዜጎች መጭበርበር መሳሪያ ሆነዋል በሚል ነው፡፡

በዙና ትሬዲንግ ተጭበርብረናል የሚሉት ወገኖች ቁጥራቸው 98 እንደሚደርስ ታውቋል፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top