Connect with us

ምጽ!…ምስኪን ህወሓት!

ምጽ!...ምስኪን ህወሓት!
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ምጽ!…ምስኪን ህወሓት!

ምጽ!…ምስኪን ህወሓት!

(በድጋሚ የቀረበ)

(እሱባለው ካሳ)

መቐለ የመሸገው የህወሓት አፈንጋጭ ክንፍ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር እህል ውሃውን ከእነአካቴው የሚበጥስ በእብሪት የተሞላ መግለጫ አውጥቶ ተመለከትኩት፡፡

አፈንጋጩ ቡድን ራሱን ሕገመንግሥቱን ጨምሮ ሕግና ሥርዓትን አክባሪ፣ ለነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ተቆርቋሪ፣ የአገር ጥቅም አስከባሪ፣ የኮሮና ወረርሽኝን በሳይንሳዊ መንገድ መካች፤ … በተቃራኒው ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ ኢ- ሕገመንግሥታዊ፣ የጦርነት አዋጅ ጎሳሚ፣ የአገር ጥቅምን አሳልፎ ሰጪ…..አድርጎ ያቀርባል፡፡

ይኸ ገራፊ፣ ደፋሪ፣ አሳዳጅ፣ ነፍስ በላ፣ የሙስናና ብልሹ አሰራር ተምሳሌት የሆነ ቡድን.. ይኸን ሁሉ ወሬውን የሚዘከዝከው አሳምሮ ለሚያውቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑ በእጅጉ ይገርማል፡፡

የሾርት ሚሞሪ ነገር… ትላንት በንጹሐን ሰዎች ክንድ የዘንዶ ጉድጓድ ልለካ እንዳላለ፣ የስንቱን ጎጆ በኢ- ሰብዓዊ ድርጊቱ፣ በግፉ እንዳልከረቸመ፣ እንዳላበላሸ፣ ቤተሰብ እንዳልበተነ… እነሆ ዛሬ 180 ዲግሪ ተከረባብቶ “እኔ ፈጣሪህ ነኝ፣ እኔ አዳኝህ ነኝ” እያለ ከመቐለ ምሽጉ ሊታበይ ይሞክራል፡፡ በንዴት፣ በብስጭት እንደተንቦገቦገ ያቅራራል፡፡ ይገርማል!!..

ለእነዚህ የደበበ ሰይፉ ግጥም ጥሩ መልስ ይሰጣል፡-

በቀበሮ ጉድጓድ – ቀበሮ መስሏቸዉ፤

ዉሾቹ አጓሩ – በዛ ጩኸታቸዉ፤

አይ የዉሾች ነገር – ማን በነገራቸዉ፤

አንበሳ እንደሆነ – የሚጠብቃቸዉ።

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top