Connect with us

“እርምጃው ይቀጥላል” ~ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን

"እርምጃው ይቀጥላል" ~ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

“እርምጃው ይቀጥላል” ~ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን

“እርምጃው ይቀጥላል” ~ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን

የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ መልዕክቶችን በሚያስተላልፉ መገናኛ ብዙኃን ላይ የሚወሰደው እርምጃ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ገለጸ።

ባለሥልጣኑ የአገርን ሠላምና የሕዝብን አንድነት የሚሸረሽሩ መገናኛ ብዙኃን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስቧል።

በቅርቡ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ሕልፈት ተከትሎ በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች በተነሳ ሁከት ዜጎች ለሞትና ለአካል ጉዳት ሲዳረጉ በርካታ ንብረትም ወድሟል።

ክስተቱን ሁሉም የአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን በሚባል ደረጃ በስፋት ሲዘግቡትም ተስተውሏል።

የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዱዓለም ለኢዜአ እንደገለጹት መገናኛ ብዙኃኑ ለዓመታት ከነበሩበት ጫና ወጥተው በነጻነት እንዲዘግቡና የሕዝቡን ሐሳብ እንዲያስተላልፉ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

ይሁን እንጂ ይህን ነጻነት በአግባቡ የማይጠቀሙና የጋዜጠኝነትን ስነ-ምግባር የሚጥሱ መገናኛ ብዙኃን መፈጠራቸውን ጠቁመዋል።
በመሆኑም የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ሽፋን በማድረግ የዜጎችን ሠላምና አብሮነት የሚሸረሽሩ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ የነበሩ ኦ.ኤም.ኤን እና ድምፀ ወያኔ ጣቢያዎች መታገዳቸውን ገልጸዋል።
የትግራይ ቴሌቪዥን ጣቢያም ስርጭቱ እንዲቋረጥ በመንግስት እርምጃ እንደተወሰደበት አስታውሰዋል።

ላም ለማስከበር ከወሰደው እርምጃ ጎን ለጎን መገናኛ ብዙኃኑን ተጠያቂ በማድረግ ረገድ ባለሥልጣኑ አዋጁ በሚፈቅድለት ሕግና ደንብ መሠረት ኃላፊነቱን የሚወጣበትና የማይታገስበት ጊዜ መሆኑን አቶ ወንድወሰን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

መገናኛ ብዙኃን ድንጋይ መወራወሪያ ሳይሆን ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅሙ ሐሳቦች የሚፋጩባቸውና ሃሳብ የሚያሸንፍባቸው ሊሆኑ ይገባልም ብለዋል።

ሕዝቡ እውነተኛና ትክክለኛ መረጃ እንዲኖረው ከማድረግ ይልቅ መቃቃርን የሚሰብኩ የመገናኛ ብዙኃን አሁንም መኖራቸውን ባለሥልጣኑ መታዘቡን አቶ ወንድወሰን አንስተዋል።

የአንድ ወገንና ቡድንን ፍላጎት በሚያንጸባርቁና የተቋቋሙበትን ዓላማ በሚዘነጉ መገናኛ ብዙኃን ላይ አሁንም የእርምት እርምጃ የመውሰድ ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የችግራቸው መጠን ቢለያይም የመፍትሄ አካል ከመሆን ይልቅ የችግሩ አካል የመሆን አዝማሚያ በመገናኛ ብዙኃኑ እንደሚስተዋልም ጠቁመዋል።

ይህንን ከመሠረቱ ለማስቀረት ባለሥልጣኑ ሕግን በማስከበር መገናኛ ብዙኃኑ በትክክለኛ መንገድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ያደርጋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ 72 የማኅበረሰብ፣ የግል /የንግድ/ እና የሕዝብ ራዴዮ ጣቢያዎች እንዲሁም 37 የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አሉ።(ኢዜአ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top