Connect with us

“በሃጫሉ ግድያ ውስጥ እጃችን የለበትም” ~ ጃልመሮ

"በሃጫሉ ግድያ ውስጥ እጃችን የለበትም” ~ ጃልመሮ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

“በሃጫሉ ግድያ ውስጥ እጃችን የለበትም” ~ ጃልመሮ

ኩምሳ ድሪባ (ጃልመሮ) የኦነግ ሰራዊት የምዕራብ ዞን አዛዥ ከ አሜሪካ ድምፅ ራድዮ ባልደረባ ጋዜጠኛ ከፅዮን ግርማ ጋር ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በቴሌፎን አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ አድርጓል።

ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን የገደለው ኦነግ ሸኔ መሆኑን ተጠርጣሪዎች ከሰጡት ቃል አረጋግጫለሁ በሚል መንግሥት የሰጠውን መግለጫ ጃልመሮ አስተባብሏል። ጃልመሮ በዚህ ምላሹ “ኦነግ ሸኔ” የሚባል ሰራዊት መኖሩን እንደማያውቅ እና እሱ የሚመራው ጦር የኦነግ ክንፍ መሆኑን ከጠቆመ በኋላ በሃጫሉ ግድያ ውስጥ እጃቸው እንደሌለበት በመናገር ለግድያው ራሱ መንግሥትን ተጠያቂ አድርጓል። በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በንፁሀን ዜጎች ላይ የተፈጠረው ኢ- ሰብአዊ እልቂት በእነሱ እንዳልተፈፀመም ተናግሯል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት የለም” የሚለው ጃልመሮ ትግላቸው ከታጠቀ የመንግሥት ጦር ጋር እንጂ ከሲቪል ንፁሀን ዜጎች ጋር አለመሆኑን ገልጿል።

በሌላ በኩል አቶ ታዬ ደንደአ የኦሮምያ የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጫካ ውስጥ ተቀምጦ የሚያተራምስ የሽፍታ ቡድን ድምፃዊ ሀጫሉን “እኔ ገድዬዋለሁ” ብሎ እንዲያምን አይጠበቅም በማለት ቃላቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ሰጥተዋል። ከዚህ ቀደምም ኦነግ በህዝብ ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ወንጀሎች ህብረተሰቡ እያወቀ በተመሳሳይ ሁኔታ አልፈፀምንም ማለታቸውን አቶ ታዬ አስታውሰዋል።

ጃልመሮ በተለይ የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማን እንደፈፀመው በነፃ ወገኖች እንዲጣራ ጠይቋል። የ50 አመቱ ጎልማሳ ጃልመሮ የምእራብ ኦሮምያን የኦነግ ጦር ላለፉት ሁለት አመታት እንደሚመራ ለአሜሪካ ድምፅ ማረጋገጡን በዘገባው ተጠቅሷል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top