Connect with us

“ኢትዮጵያ ከዚህ በላይ ከባድ ፈተና አይገጥማትም!”

"ኢትዮጵያ ከዚህ በላይ ከባድ ፈተና አይገጥማትም!"
Photo: Facebook

ፓለቲካ

“ኢትዮጵያ ከዚህ በላይ ከባድ ፈተና አይገጥማትም!”

የገጠሙን እጅግ ከባድ ፈተናዎች ወደ ወሳኝ ምእራፍ በር ይሆናሉ። ኢትዮጵያ ምናልባት ከፋሽስት ወረራና ከአድዋ ድልና ከዚያድባሬ ወረራ በኃላ ከውስና ከውጭ እጅግ ከባድ ፈተና የገጠማት ዘመን ይህ ጊዜ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ወደ ወሳኝ የሰላም የዴሞክራሲና የብልጽግና ምዕራፍ ለመሻገር ወሳኝ ውሳኔዎች ድሎች ተገኝተዋል:-

❶. በኢትዮጵያውያን ጥረትና ላብ የተገነባው የህዳሴ ግድብ ከምርጥ የዲፕሎማሲያዊ ቼዝ ጌም ወደ አፍሪካ ህብረት በመመለስ ድል ጋር ውሃ ሙሌቱ ተጀምሯል። ግብጽ ማምሻውን የመጨረሻ ሸንፈቷን በአንድ ስንሽ “ሙሌቱ እኔን የጎዳኝ ለታ ያኔ እንተያያለን!” በሚል ምንም ያለማድረግ የሽንፈት መልስ ተሸንፋለች። ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው።

❷.እጅግ አደገኛ መዥገር ህውሃት ተሽቀንጥራ መቛለ ከከተመች ሰነበተች። ሴራዋም እንደጠበቀችው ባለመሆኑ የገዛ የትግራይ ህዝብ ልትወረር ነው በሚል ጭንቀቷን በጩኸት ብታቀልጠውም አብይ ባላሰበችበት ጉንጓን ውስጥ ከቷታል። የአብይ ቀጣይ የሴራ ደምስሮቿን መበጣጠስ ከማሴር ወደ መከላከል ድል ተጎናጽፏል።

❸.ከመጀመሪያው ጀምሮ በኢትዮጵያዊነት እና አፍሪካዊነት በተሰራው ግንባርቀደም ስራ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጠንካራ የኮረና መከላከልና መቆጣጠር የጤና ስርአትና አቅም ከፈጠሩ #5 አገራት አራተኛ ለመሆን በቅታለች። አብይ ይችላል ስንል በትብታብ ውስጥም መፍትሄ አለው ማለታችን ነው።

❹. ባለፉት 50 አመታት አንድ ጠብ የሚል የድልና ነጻነት ታሪክ የሌለው ሼኔ ኦነግ ዛሬም ነጻ አውጪ ነው። በሚችለው የዝንጀሮ ትግል በአብይ ቸልተኝነትና የይመለሳሉ ተስፋ ጫካ ቢገባም የገዛ ወገኑን በመግደል የሽብሩ የመጨረሻውን ሴራ በጠንካራ አመራር ከሽፏል። በመቀጠል ከባድ ፍርድና ድባቅ ይጠብቀዋል። ለማየት ያብቃን።

❺. የኢትዮጵያ እንቁ ልጅ በሴረኛው ሸኔ ቢገደልም ቀጥሎም በ10ቀን አገርን አተራምሶ ስልጣን ለመቀማት ቢታሰብም ሰውየው የተካነው ፈተናዎችን በመቀልበስ የድል ችቦ በመለኮስ ነውና በምን ታመጣላቹሁ ያዙኝ ልቀቁኝ ባይና የጽንፈኛ ቡድን ተከርቸም ከቶ በተለያዩ ወኔጀሎች የተሳተፉ ከ4ሺ በላይ ጋሻጃግሬን አደብ አስገዝቶ በውስጡ የነበሩ ከ524 በላይ አመራርና ፖሊስ በተጠያቂነት ዘብጥያ ከቷል። ጅል ከመምሰል ኮስተር ማለት እንዲህ ነው።

ኢትዮጵያውያን እድለኛ ነን። በሚችል መሪ ከባድ ፈተናን ተሻግረን የንጋት ኮኮብ ለማየት እየተቃረብን ነውና ከአብይና ከብልጽግና መርከብ ተሳፍረን ካሰብንበት እንደርሳለን።

(ምንጭ :-የኦሮምያ ብልፅግና ፓርቲ)

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top